እስከ 5 ዓመት እስራት የሚያስቀጣው አዲሱ

- Advertisement -
Sidebar AD

የመረጃ ነጻነት አዋጅ

#Ethiopia | የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለዓመታት ሲጠበቅ የነበረውን አዲሱን “የመረጃ ነጻነት አዋጅ” በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ይህ አዲስ ሕግ ቀደም ሲል ከነበረው አሠራር በተለየ መልኩ ከመንግሥት አካላት በተጨማሪ የግል ድርጅቶችም መረጃ የመስጠት ግዴታ እንዲኖርባቸው አድርጎ ያሻሻለ ሲሆን፣ የመንግሥት ፕሮጀክቶችን ዝርዝር አፈጻጸምና ውጤት ለሕዝብ ይፋ ማድረጋቸውን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ድንጋጌ አካቷል።

በተጨማሪም፣ መገናኛ ብዙኃን የሕዝብ ጥቅም መረጃዎችን ሲጠይቁ ከማንኛውም የማባዣ ወጪ ክፍያ ነፃ እንዲሆኑ ተደንግጓል።

የዚህ አዋጅ ትልቁ መነጋገሪያ ጉዳይ መረጃን በደበቁ ወይም ባሻጠሩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ላይ የጣለው ጠንካራ የወንጀል ቅጣት ነው።

ሆን ብሎ መረጃን ያጠፋ፣ ያበላሸ፣ የደበቀ፣ ሙስናን ለመሸፈን በሚስጥር የያዘ ወይም የሀሰት ሰነድ ያዘጋጀ ኃላፊ ጥፋተኝነቱ በፍርድ ቤት ሲረጋገጥ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና እስከ 100 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ (ወይም በሁለቱም) ይቀጣል።

እንዲሁም ሆን ብሎ የተሳሳተ መረጃ የሰጠ፣ ያለበቂ ምክንያት ትዕዛዝ ያልፈጸመ ወይም የመከላከያ ምስጢር አሳልፎ የሰጠ አካል እስከ 3 ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት እንደሚቀጣ ተደንግጓል።

በተጨማሪም መረጃ የመጠየቅ መብትን በቸልተኝነት ለሚያደናቅፉ አካላት ማለትም የቃል ጥያቄን በቅጽ ለመሙላት ፈቃደኛ ካለመሆን፣ መረጃን አትሞ ካለማውጣት፣ እና ለአካል ጉዳተኞች ምቹ በሆነ መንገድ መረጃን ተደራሽ ካለማድረግ ጋር የተያያዙ ጥፋቶች እስከ 1 ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት እና እስከ 50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ያስቀጣሉ።

ይህ አዋጅ በሀገሪቱ ግልፅነትን፣ ተጠያቂነትን እና የሕግ የበላይነትን ለማስፈን ትልቅ እመርታ መሆኑ ተገልጿል።

Ethiopia Insider

#Ethiopia #InformationFreedom #BreakingNews #Transparency #Accountability #EthiopianParliament #MediaFreedom #LawAndJustice


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: