#Ethiopia | ተስፋዬ የለውዝ እና ሰሊጥ ቅቤ ማምረቻ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በሰጠው የጥራት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።
ድርጅቱ በተለያዩ የምርት ዓይነቶች ላይ የተቀመጡ የጥራት መስፈርቶችን ማሟላቱ በጥራት ማረጋገጫ ኦዲት ሂደት ተገምግሞና በፍተሻ ላቦራቶሪ ተረጋግጦ የተሰጠው መሆኑን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አስታውቋል።
የሰርቲፊኬሽን ሂደቱ በISO/IEC 17065 ዓለም አቀፍ የምርት ጥራት ሰርቲፊኬሽን አሰራር ሥርዓት መሰረት የተከናወነ ነው።
ሰርቲፊኬቱን የኢተምድ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢንጂነር መዓዛ አበራ ለድርጅቱ ባለቤት ለሆኑት ለተስፋዬ አስረክበዋል።
በርክክብ ፕሮግራሙ ላይ ክብርት ኢንጂነር መዓዛ አበራ፤ የምርትና አገልግሎት ጥራት በገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን፣ ደንበኛን ለማርካት፣ አሠራርን ለማሻሻልና ውጤታማነትን ለማስቀጠል ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። “ይህንን የምርት ሰርተፊኬት ማግኘታችሁ እንደ ተቋም ለጥራት ያላችሁን ቁርጠኝነት ያሳያል” በማለት፣ ተቋማቱ በጥናትና ምርምር የተደገፈ የተሻለ ምርትና አገልግሎት ማቅረብ እንዲችሉ በምርት የጀመሩትን ጥራትን የማስጠበቅ ሂደት በአሰራር ሥርዓትም ማስቀጠል እንዲችሉ አሳስበዋል።
ተስፋዬ የለውዝ እና ሰሊጥ ቅቤ ማምረቻ ድርጅት፣ የሀገር ውስጥ ገበያን ለማርካት ከፍተኛ ጥራት ያለው የምርትና አገልግሎት ለማቅረብ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።
ድርጅቱ፣ ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የተሰጠው የጥራት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት፣ የምርቱን ጥራት ለማስጠበቅ እና ለደንበኞቹ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያደርገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑን አመልክቷል።
መደምደሚያ …
ተስፋዬ የኦቾሎኒ ቅቤ ማምረቻ ድርጅት
(Tesfaye Peanut Butter Manufacturing)
በኦሮሚያ ክልል፣ ፍቼ ከተማ ይገኛል።
የብሔራዊ ደረጃዎች አጠቃቀም ፈቃድ
(Ethiopian Standards Mark License)፦
ድርጅቱ ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት (IES) የብሔራዊ ደረጃ ምልክትን ለመጠቀም የሚያስችለውን ፈቃድ (በቁጥር IES-CSMA/ESM662/2018) አግኝቷል።
የአፍሪካ የደረጃዎች ድርጅት (ARSO) ዕውቅና፦
ድርጅቱ የቀጣናዊ ትስስርን እና የንግድ እንቅስቃሴን ለማገዝ ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት እና ከአፍሪካ የደረጃዎች ድርጅት (ARSO) የጋራ የጥራት ምልክት (Quality Dual Marks) ዕውቅና ሰርቲፊኬት ተበርክቶለታል።
የምርት ጥራት ማረጋገጫ (Product Certification)፦ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ECAE) በተለያዩ የምርት ዓይነቶች የጥራት መስፈርቶችን ላሟሉ ድርጅቶች የጥራት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት በሰጠበት ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝቶ ሰርተፍኬቱን ተረክቧል። ሂደቱም በISO/IEC 17065 ዓለም አቀፍ የምርት ጥራት ሰርቲፊኬሽን አሰራር ሥርዓት መሰረት የተከናወነ ነው።



Source: GetuTemesgen









No comments yet.