‎ሜፀር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተከሰተው ድንገተኛ የጤና እክል በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | ​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ አሪ ወረዳ ሜፀር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በዛሬው ዕለት በተከሰተ ድንገተኛ የሕመም ስሜት ሳቢያ ራሳቸውን የሳቱና የማስመለስ ምልክት የታየባቸው በግምት እስከ 200 የሚደርሱ ተማሪዎች ወደ ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመግባት አስቸኳይ የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ሆስፒታሉ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

‎የሆስፒታሉ የሕክምና ባለሙያዎች በሙሉ አቅማቸው ባደረጉት ፈጣንና ያልተቆጠበ ጥረት አብዛኞቹ ተማሪዎች በአሁኑ ወቅት በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።

‎ከተማሪዎቹ መካከል ከፍተኛ ክትትል የሚያስፈልጋት አንዲት ተማሪ ብቻ ለተሻለ ሕክምና እና ጥንቃቄ ሲባል ወደ ጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የተላከች ሲሆን፣ እስካሁን ባለው መረጃ ሕይወቱ ያለፈ ምንም ተማሪ አለመኖሩን የሆስፒታሉ አስተዳደር በይፋ አረጋግጧል።

‎​ይህን ድንገተኛ ሕመም የቀሰቀሰው መንስኤ ምን እንደሆነ ከተወራው የጁስ ዱቄት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ መሆኑን ለማረጋገጥ የሕክምና ባለሙያዎችና የሕብረተሰብ ጤና ቡድኑ በጥልቀት ምርመራ እያደረጉ ይገኛሉ።

‎የላብራቶሪና የሙያዊ ምርመራው ውጤት ተጠናቆ እውነታው ይፋ እስኪሆን ድረስ ማኅበረሰቡ በትዕግሥት እንዲጠባበቅ የጠየቀው ሆስፒታሉ፣ ሁኔታው ሙሉ በሙሉ በሕክምና ባለሙያዎች ቁጥጥር ሥር በመሆኑ ወላጆችና የአካባቢው ነዋሪዎች ያለምንም መደናገጥ ራሳቸውን እንዲያረጋጉ ጥሪ አቅርቧል። በተጨማሪም ተማሪዎቹን በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም በማምጣት ረገድ ለታየው የሕዝብ ትብብር ሆስፒታሉ ምስጋና አቅርቧል።

‎ጌትነት ተመስገን
‎Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

‎#getutemesgen #getu #ጌጡ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: