ኢትዮጵያ አዲስ ባንክ ልትቀላቀል ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራት የጋራ መሠረት የሆነውን የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክን እንድትቀላቀል የተዘጋጀውን የማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱ ተገለጸ።

ይህ ታሪካዊ እርምጃ ሀገራችን በዓለም አቀፍ የፋይናንስ መድረክ ላይ ያላትን ተደራዳሪነትና አማራጭ የመምረጥ አቅም በእጅጉ የሚያጠናክር ሲሆን እንደ ዓለም ባንክና አይ ኤም ኤፍ ካሉ ተቋማት ውጪ ያለምንም የፖለቲካ ቅድመ-ሁኔታና የሀገራትን ሉዓላዊነት ሳይጋፋ ግዙፍ የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የሚያስችል ትልቅ ስትራቴጂካዊ ጉዳይ ነው።

በተለይም በባንኩ ውስጥ የፕሮጀክቶች ማፅደቅ ሂደት እጅግ ፈጣን መሆኑና ከ18 እስከ 24 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ መጠናቀቁ ለሀገራዊ ልማታችን ቀልጣፋና ተመራጭ አማራጭ ይዞ የመጣ ነው።

​የዚህ ታላቅ ባንክ አባል መሆን ለኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ በርካታ መዋቅራዊ ጥቅሞችን የሚያስገኝ ሲሆን ባንኩ ብድሮችን በዶላር ብቻ ሳይሆን በአባል ሀገራቱ የሀገር ውስጥ ገንዘብ (ለምሳሌ በቻይና ዩዋን) የሚያቀርብ በመሆኑ በሀገራችን ያለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረትና የዶላር መዋዠቅ የሚያስከትለውን የዕዳ ጫና በእጅጉ ያቃልላል። ይህ አስተማማኝ የፋይናንስ አቅርቦት እንደ ግብርና ዘመናዊነት፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት፣ የታዳሽ ኃይል ማመንጫዎች እና ለዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ፕሮጀክቶች የሚውል የረጅም ጊዜ ካፒታል በቀላሉ ለማግኘት ታላቅ ዕድል ይፈጥራል።

​ከዚህ ባለፈም ስምምነቱ አዲስ ለተጀመረው የሀገር ውስጥ የካፒታል ገበያ የቦንድ ሽያጭና የፋይናንስ ዋስትናዎችን በመስጠት ረገድ የላቀ አቅም የሚፈጥር ሲሆን የቴክኒክ ድጋፍና የእውቀት ሽግግርን በማመቻቸት ተቋማዊ አቅማችንን በከፍተኛ ደረጃ ይገነባል።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክን ለመቀላቀል እያደረገችው ያለው ስኬታማ ጉዞ ከብሪክስ አባል ሀገራት የምታገኘውን ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትና የንግድ ትስስር ወደ ላቀ ከፍታ የሚያሸጋግር ነው ተብሏል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: