ኢትዮጵያ ጥይት ወደ ውጭ መላክና ወደ ሀገር ውስጥ ዶላር ማስገባት ጀመረች።የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት በሀገር ውስጥ የተመረቱ የ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ኢትዮጵያ ጥይት ወደ ውጭ መላክና ወደ ሀገር ውስጥ ዶላር ማስገባት ጀመረች።
የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት በሀገር ውስጥ የተመረቱ የጦር መሣሪያ ጥይቶችን ለጎረቤት ሀገራት መላክ መጀመሩን አስታውቋል።
ይህ አዲስ ጅምር ለሀገሪቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ ሲሆን፣ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች ምርቱን በራስ አቅም ማምረታቸው ቀደም ሲል የነበረውን የውጭ ጥገኝነትና ከፍተኛ ወጪ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት አስችሏል።
አሁን ላይ ምርቶቹን ለኤክስፖርት ማብቃት መቻሉ የኢትዮጵያን የማምረት አቅም ዕድገት የሚያሳይና ለኢኮኖሚዋም ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት ነው።
ከዚህ ባለፈም ሀገሪቱ የድሮን እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂዎችን በማልማት የጸጥታ መዋቅሯን በከፍተኛ ሁኔታ እያዘመነች ትገኛለች።
በቀጣዮቹ ዓመታትም ከቀላል ጥይቶች ባሻገር የተለያዩ የጦር መሣሪያ አካላትን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እየተሠራ ሲሆን፣ ሂደቱ በትክክል ከተጠናከረ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑት የመከላከያ ኢንዱስትሪ ማዕከላት አንዷ እንደምትሆን ይጠበቃል።
Via የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: