🇨🇻
#FIFAWorldCup | ኬፕ ቨርዴ በምድብ H የመጨረሻ ጨዋታዋ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር 0-0 አቻ በመለያየት፣ በ3 ነጥብ ወደ 16 ቡድኖች ጥሎ ማለፍ መብቷን አረጋግጣለች።
በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ የተሳተፈችው ምዕራባዊቷ የአፍሪካ ደሴት ሀገር ኬፕ ቨርዴ፣ ሦስቱንም የምድብ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት በማጠናቀቅ ታሪካዊ ስኬት አስመዝግባለች።
በሌላው የምድብ H ጨዋታ ስፔን ኡራጓይን 1-0 በማሸነፍ በ7 ነጥብ የምድቡን መሪነት ይዛ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች። የስፔንን ብቸኛ የድል ግብ አሌክስ ባዬና አስቆጥሯል።
በዚህ ውጤት መሠረት ስፔን እና ኬፕ ቨርዴ ወደ 16 ቡድኖች ጥሎ ማለፍ ሲቀላቀሉ፣ ኡራጓይ እና ሳዑዲ አረቢያ ከውድድሩ ተሰናብተዋል።
Source: GetuTemesgen









No comments yet.