የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ፣ የመምሪያዎች አመራር እና አባላት፣ የአስተዳደር ኃላፊዎች፣ የተለያዩ የአካባቢው ነዋሪዎችና ታዛቢዎች ተግኝተዋል።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ቡልጋሪያ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በተለያየ ጊዜ የተሰበሰበ ከ6ሺህ በላይ የሺሻ ዕቃ እና 10 ኪሎ ግራም ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ ዕጽ ተወግዷል።
በቦታው የተገኙት የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የወንጀል መከላከል እና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ብስራት ታደለ ሺሻ እና አደንዛዥ ዕጽ መጠቀም የትውልዱን ስነ ልቦና የሚጎዳ ነው ብለዋል። በሌላ መልኩ ለወንጀል መፈጸም መንስኤ መሆኑን በመረዳት በተለያየ ጊዜ የተሰበሰበ ከ6 ሺህ በላይ የሺሻ ዕቃ እና 10 ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕጽ መወገዱን ገልጸዋል። ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም መምሪያ አዛዡ ጠቁመዋል።
የክ/ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ቁጥጥሩ እና እርምጃው ደንብን የሚመለከት ቢሆንም ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር የኦፕሬሽን እና የማስወገድ ስራ እንደሚሰራ አመላክተዋል። በሚሰራው ሺሻ ዕቃ መሰብሰብ ተግባር ማህበረሰቡ ትልቅ አቅም በመሆኑ ወደፊትም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ጠቅሰዋል።
ጽ/ቤታቸው ለክፍለ ከተማው ብሎም ለከተማው ሠላም መስፈን የቆመ ስለሆነ በአዋኪ ድርጊቶች ላይ በትኩረት እንሰራለን ሲሉ የተናገሩት ደግሞ የሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ታዬ ሽፈራው ናቸው።
በዕለቱም በርካታ ቁጥር ያለው የሺሻ ዕቃ እና አደንዛዥ ዕጽ በጋራ መወገዱን አንስተው ብዙ ወጣቶች ከሱስ እንዲላቀቁ ትምህርት ይሰጣል ብለዋል።
የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የወንጀል ምርመራ መምሪያ ኃላፊ ተወካይ ዋና ኢንስፔክተር ስለሺ ሸንቁጤ የሺሻ እቃው እና አደንዛዥ ዕጹ የክትትል እና የምርመራ ቡድን በማቋቋም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን የተሰበሰበ መሆኑን ገልጸዋል። በጉዳዩ ዙሪያ መዝገብ ጭምር መደራጀቱን ዋና ኢንስፔክተር ስለሺ ተናግረዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው እርምጃው ተገቢ መሆኑን በማንሳት ለፖሊስ የሚሰጡትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።



Source: Yeneta Tube








No comments yet.