የቡና ኮንትሮባንድን ለመግታት እስከ 50 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣትና የንብረት መወረስ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት በሆነው የቡና ምርት ላይ የሚፈጸመውን ህገ-ወጥ ዝውውር (ኮንትሮባንድ) ለመግታት፣ ከተባባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት እጅግ ጥብቅ የሆኑ የቁጥጥርና የቅጣት እርምጃዎችን መተግበር መጀመሩን አስታወቀ።
የቡናና ሻይ ባለስልጣን የዋና ዳይሬክተር ፅህፈት ቤት ሀላፊ ዶር ሰፊሳ አባቡ እንደተናገሩት ህገ-ወጥ የቡና ንግድ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ በእጅጉ እየጎዳ በመሆኑ፣ ድርጊቱን በቁርጠኝነት ለመከላከል አዲስ የክትትል ስትራቴጂ ተቀርጾ ወደ ስራ ተገብቷል
በዚህም መሠረት ባለስልጣኑ ህገ-ወጥ የቡና ዝውውርን ለማስቆም ከፌዴራልና ክልል ፖሊስ፣ ከጉምሩክ ባለስልጣን እና ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር የጋራ ግብረ-ኃይል አቋቁሞ እየሰራ ይገኛል።
በመሆኑም ያለ ህጋዊ ፈቃድና ሰነድ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ማንኛውም የቡና ምርት ሙሉ በሙሉ ይወረሳል።
በህገ-ወጥ የቡና ሰንሰለት ውስጥ ተሳትፈው በሚገኙ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ ም እንደ ጥፋታቸው ደረጃ እስከ 50 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ከባድ የገንዘብ ቅጣት ይጣላል።
የኬላዎች ቁጥጥርን በተመለከተም በመረጃዎችን በፈጣን ቴክኖሎጂ በመለዋወጥ፣ በዋና ዋና የቡና አምራች ክልሎችና መውጫ ኬላዎች ላይ ፍተሻዎች ተጠናክረዋል ሲሉ ዶ/ር ሰፊሳ ተናግረዋል::
የኮንትሮባንድ ቁጥጥሩ ውጤታማ የሚሆነው ከመነሻው ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለገበያ ማቅረብ ሲቻል ነው” ያሉት ኃላፊው፣ ምርቱ መሬት ላይ እንዳይሰጣ እና በአልጋ ላይ እንዲደርቅ የማስተማርና የመደገፍ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተያያዘም የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ በማድረስ በሄክታር የሚገኘውን ምርት ማሳደግ የተቻለ ሲሆን፣ ይህ ጥራት ያለው ምርት በኮንትሮባንድ እንዳይባክን የቁጥጥር ስራው ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል
@Seledadotio

No comments yet.