” የሻምበል አበበ ቢቂላ ውድድር ማራቶን ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያውያን የጽናትና የድል ታሪክ ማደሻ እንዲሁም ማስታወሻ መድረክ ነው።”
#Ethiopia | የሁለት ጊዜ የኦሊምፒክ ማራቶን ሻምፒዮና እና ለአፍሪካ አትሌቲክስ ፈር ቀዳጅ የሆነውን ታላቅ የባዶ እግር ገድል የሚዘክርና በሀገሪቱ የስፖርት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ ውድድር ነው።
በዚህ ታላቅ ዓመታዊ መድረክ ላይ ከ12 ክለቦች፣ ከ4 ክልልሎች፣ ከየአካባቢው የተውጣጡ በርካታ ጀማሪና ልምድ ያላቸው ከ300 በላይ የረጅም ርቀት አትሌቶች ይሳተፋሉ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዚህ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ምልክት የሆነውን ታሪካዊ ጀግና ከመዘከር ባለፈ፣ የቀጣዩን ትውልድ ስመ-ጥር አትሌቶች ለማፍራት ትልቅ መነሻ በማድረግ ላለፉት 41 ዓመታት በሻምበል አበበ ቢቂላ ስም ሲያዘጋጅ ቆይቷል።
ነገ በሐዋሳ ውብ ጎዳናዎች ገና የማለዳው የፀሐይ ጮራ ሰማዩን በብሩህ ወርቃማ ቀለም መፈንጠቅ ሲጀምር፣ በመቶዎች በሚቆጠሩ የዘመናችን ኮከብ አትሌቶች በፈጣን እግሮቻቸው ሊፋለሙ ቀጠሮ ይዘዋል።
ከተለያዩ አካባቢዎች ተሰባስበዉ ለአንድ ዓላማ የሚሮጡ አትሌቶች የጀግናውን የአበበ ቢቂላን ፈለግ ለመከተል ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።
ባለፈው ዓመት በተደረገው 41ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ውድድር ላይ ድንቅ ሰዓት አስመዝግበው ከአንደኛ እስከ አስረኛ የወጡ አትሌቶች የሚከተሉት ነበሩ፦
በወንዶች መድረክ
| ደረጃ | የአትሌቱ ስም | የተመዘገበ ሰዓት | የሚወክልበት ክለብ
1 ገመቹ ያደሳ 2:12.43 ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ
2 ፲አለቃ ጋዲሳ ታጀበ 2:13.40 መቻል
3 አሰፋ ተፈራ 2:14.12 ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ
4 ደርቤ ሮቢ 2:14.23 ፌደራል ፖሊስ
5 ማሞ መንግስቱ 2:15.05 ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ
6 ፅዳት አበጀ 2:15.12 ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ
7 ፶አለቃ ሸንጎ ከበደ 2:15.15 | መቻል
8 መ/ወ/ር ጥላሁን ስሜ 2:15.32 (?)
9 አብዱላሒ% ሙሳ 2:16.03 በግል
10 ሙለታ ዴሲሳ 2:16.11 ኦሮሚያ ፖሊስ
በሴቶች ምድብ
| ደረጃ | የአትሌቱ ስም | የተመዘገበ ሰዓት | የሚወክልበት ክለብ
1 መሠረት ገብሬ 2:40.50 ኦሮሚያ ክልል
2 ፲/አ አሹማር ዘበናይ 2:43.15 | መቻል
3 ም/፲/አ አስመሬ በየነ 2:43.18 መቻል
4ትዕግስት ጌትነት 2:43.27 ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ
5 ፶/አ አበበች አፈወርቅ 2:43.37 መቻል
6 ም/፲/አ መልኪቱ ወርቅነህ 2:43.37 መቻል
7 መሠረት ሒርጳ 2:44.09 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
8 ፶/አ ዘርፌ ልመንህ ተሰማ 2:44.20 | መቻል
9 ዓለም ገ/እግዚአበሔር 2:45.21 | መቻል
10 ከምላክ ፋንታሁን 2:45.25 አዲስ አበባ
ነገ ማለዳ የሐዋሳ ፀሐይ ስትፈነጥቅ፣ አዲሶቹ የዘመናችን ኮከቦች የታሪካዊውን ጀግና ፈለግ በመከተል አዲስ ታሪክ ለመጻፍ በጉጉት ይጠበቃሉ።
ለመላው ተፎካካሪዎች መልካም ዕድል!
ቻይና አብዲ
Ethiopian Athletics Federation Amensisa Kebede Sileshi Sihin Sileshi Sihin Yemane Tsegay Sara Hassen Adem Getu Geremew Ethio runners
Source: GetuTemesgen









No comments yet.