”በጣም ደስ ብሎናል ምኞታችን ሞላ፣

- Advertisement -
Sidebar AD

አሸንፎ መጣ አበበ በቂላ”

📌ባዶ እግሩን ሮጦ ዓለምን ያስደነቀው የምንግዜውም ድንቅ አትሌት ሻምበል አበበ በቂላ

#Ethiopia | ​በዓለም አቀፍ የስፖርት ታሪክ ውስጥ ስሙ በወርቅ ፊደላት የተጻፈውና የኢትዮጵያ ኩራት የሆነው ሻንበል አበበ በቂላ ለአፍሪካ አህጉር በኦሊምፒክ መድረክ የመጀመሪያውን ወርቅ ያስገኘ ድንቅ የኢትዮጵያ ልጅ ነው።

ይህ ድንቅ አትሌት በተለይ በ1960 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) በሮም ኦሊምፒክ የተካሄደውን የማራቶን ውድድር ባዶ እግሩን በመሮጥና በአንደኝነት በማጠናቀቅ መላውን ዓለም ያስደነቀ ሲሆን ድሉም ጥቁር ሕዝቦች በዓለም መድረክ ላይ ያላቸውን ታላቅ የጽናትና የአሸናፊነት አቅም በተግባር ያሳየ ታሪካዊ ክስተት ነበር።

​ከዚህ ታላቅ ስኬት በኋላም አትሌት አበበ በቂላ በ1964 ዓ.ም በቶኪዮ ኦሊምፒክ የራሱን የዓለም ሪከርድ በማሻሻል ለሁለተኛ ጊዜ ተከታታይ የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን ይህም በኦሊምፒክ ታሪክ የማራቶን ድልን በተከታታይ በመውሰድ የመጀመሪያው ስፖርተኛ አድርጎታል።

በወቅቱ የኢትዮጵያ ክብር ዘበኛ አባል የነበረው አበበ በቂላ በስፖርቱ ዓለም ላሳየው ተወዳዳሪ የሌለው ጽናትና ለሀገሩ ባበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሻምበልነት ማዕረግ የተሰጠው ሲሆን ዛሬም ድረስ ለቀጣዩ የአፍሪካና የዓለም አትሌቶች ትውልድ የመንፈስ ጥንካሬና የድል ፈር ቀዳጅ ተምሳሌት ሆኖ በክብር ይነሳል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለዚህ ጀግና መታሰቢያው ይሆን ዘንድ በእርሱ ስም የሚያሰናዳው ”42ኛው የሻ/ል አበበ በቂላ ማራቶን ውድድር በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ማለዳ እንዲጀመር ቀጠሮ ቢያዝለትም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ወደ 5:00 ሰዕት ተሸጋሽጓል።

ዝግጅት ክፍላችን ውድድሩን ለመዘገብ በስፍራው የተገኘ ሲሆን ለሁሉም አትሌቶች
መልካም ምኞታችንን እንገልጻል።

ለ Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን) ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽንስ

ያፌት ገ/ህይወት
ከሲዳማ ፤ ሐዋሳ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2