ህወሃት ምላሽ ሰጠ‹‹በትግራይ ዙሪያ የድሮን ክትትሉ ቀጥሏል›› ሕወሓትሕወሓት ወታደራዊ ግዳጅ እየፈጸመ መሆኑን ካደ፡፡ ቡድኑ የ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ህወሃት ምላሽ ሰጠ‼️
‹‹በትግራይ ዙሪያ የድሮን ክትትሉ ቀጥሏል›› ሕወሓት‼️
ሕወሓት ወታደራዊ ግዳጅ እየፈጸመ መሆኑን ካደ፡፡ ቡድኑ የአውሮፓ ህብረት ያወጣውን ማሳሰቢያ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ፣ መሬት ላይ ያሉ እውታዎችን በመካድ፤ የፌዴራል መንግስቱ ላይ ተጨማሪ ክሶችን አቅርቧል፡፡
ህወሓት በኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረት ልዑክ በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያወጣውን መግለጫና የሰነዘረውን ወቀሳ ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ጠንከር ያለ ይፋዊ ምላሽ ሰጥቷል። የአውሮፓ ሕብረት ልዑክ ህወሓት “ትይዩ ክልላዊ ምክር ቤት አቋቁሟል” እና “የግዳጅ ውትድርና ምልመላ እያካሄደ ነው” በማለት የሰነዘረውን ወቀሳ ያጣጣለው ድርጅቱ፣ ሕብረቱ መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ እውነታ ወደ ጎን በመተው በተሳሳተ መረጃ ላይ የተመሠረተ መግለጫ አውጥቷል ሲል ኮንኗል።
ህወሓት በትግራይ ውስጥ “ትይዩ ክልላዊ ምክር ቤት” አቋቁሟል የሚለው ወቀሳ ሙሉ በሙሉ መሠረተ ቢስ ነው ብሏል። በትግራይ ሕዝብ ስም የተቋቋመ ሌላ አዲስ ምክር ቤት እንደሌለ የገለጸው ድርጅቱ፣ ቀደም ሲል በሕግ የተመረጠው ብቸኛው የትግራይ ክልላዊ ምክር ቤት ከከተሞች እስከ ገጠር ማኅበረሰብ ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ወደ መደበኛ ሥራው መመለሱንና ይህም በታችኛው መዋቅር በኩል ጭምር ተቀባይነት ያገኘ መሆኑን አስታውቋል።
ድርጅቱ አስገዳጅ ምልመላ እያካሄደ ነው መባሉ ግልጽ ያልሆነና በማስረጃ ያልተደገፈ ክስ ነው ሲል አጣጥሎታል። ይሁን እንጂ በትግራይ ዙሪያ ከፍተኛ የወታደራዊ ኃይል ስምሪት፣ ቀጣይነት ያለው የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃቶችና የአየር ላይ ክትትሎች ባሉበት ነባራዊ ሁኔታ፣ የክልሉ ባለሥልጣናት ሕዝቡን ከዳግም ጭፍጨፋና ከህልውና አደጋ የመጠበቅና ራሱን የመከላከል ሞራላዊና ሕጋዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝቧል።
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: