♦️
♦️”ኢትዮጵያ ቡና ማለት ህይወት ነው፤ሁሌ ስለ ኢትዮጵያ ቡና እናስባለን፤አንድ ቀን ደግሞ ኢት.ቡና ይበልጥ ከፍ ብሎ እናየዋለን”ኢብራሂም ሁሴን(የቀድሞ የኢት.ቡና ተጫዋች)
📌በእርግጥ በኢትዮጵያ ቡና ጎልቶ ይታይ፣ስሙ ገኖ እንጂ መብራት ኃይልና አዳማ ከተማም ኢብራሂም ሁሴን የሚለውን ስም በኢትዮጵያ እግር ኳስ እንድናውቀአንድ ቀን ደግሞ ኢት.ቡና ይበልጥ ከፍ ብሎ እናየዋለው ያደረጉ ክለቦች ናቸው፤በተለይ መብራት ኃይል ከልጅነቱ ጀምሮ ወደላይ ያሳደገው ባለውለተኛ ክለቡ ነው።
የመሃል ሜዳው አቀጣጣይ ኢብራሂም ሁሴን በድንቅ ችሎታው ብቻ ሳይሆን በዲሲፒሊኑና በፈርጣው ተክለ ሠውነቱም ተለይቶ ይታወቃል።
በአሁን ሠዓት ኑሮውን በአሜሪካ ያደረገው ኢብራሂም ሁሴን ለቀድሞ ክለቡ ኢትዮጵያ ቡና ያለው ፍቅር ዛሬም ድረስ አልደበዘዘም፤የቦታ ርቀትና የሀገር ልዩነት ለኢትዮጵያ ቡና ያለውን ፍቅር አላደበዘዘበትም፤ዛሬም ፍቅሩ ትኩስና ያልበረደ እንደሆነ ንግግሮቹ ያሳብቁበታል።
በቃ ኢትዮጵያ ቡና በልቤ ውስጥ አለ፣እንደውም ለእኔ ኢትዮጵያ ቡና ማለት ህይወቴ ነው ሲል በኩራት ስሜት ታጅቦ ይናገራል።
በአሜሪካ በሚኒሶታ ግዛት በኢትዮጵያዊያን አመታዊ የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ላይ ኢብራሂምን ድንገት የዲሲ ዩኒቲ እግር ኳስ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ሆኖ ያገኘው የሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያሉ ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ በኢትዮጵያ ቡና ዙሪያ አንስቶለት”ኢትዮጵያ ቡናን በቃላት መግለፅ ከባድ ነው፤በቃ በአጭሩ ኢትዮጵያ ቡና ማለት ህይወታችንም ማለት ነው፤ሁሌ ስለ ኢትዮጵያ ቡና እናስባለን፤አንድ ቀን ደግሞ ኢት.ቡና ይበልጥ ከፍ ብሎ እናየዋለን፤ ይሄንንም በትልቅ ተስፋ እንጠብቃለን”ሲል የሀገርና የቦታ ርቀት ያልገደበው ፍቅር ዛሬም ድረስ በውስጡ እንዳለ አመለ ሸጋው ኢብራሂም ሁሴን ተናግሯል።
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)ከኤገን ሚኒሶታ
Source: GetuTemesgen









No comments yet.