እራሴን ችዬ እዋጋለሁ-እስራኤልየእስራኤል  መከላከያ ሚኒስትር ከኢራን ጋር ዳግም ወደ ጦርነት በቀናት ውስጥ ልንገባ እንችላለን …

- Advertisement -
Sidebar AD
እራሴን ችዬ እዋጋለሁ-እስራኤል‼️
የእስራኤል  መከላከያ ሚኒስትር ከኢራን ጋር ዳግም ወደ ጦርነት በቀናት ውስጥ ልንገባ እንችላለን አሉ።
አይ ዲ ኤፍ ዝግጅት እንዲያደርግም ትዕዛዝ ተሰጥቶታል ብለዋል ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ።
ኢራን ምንም ዓይነት ሚሳኤል ወደ እስራኤል ካስወነጨፈች አፀፋው የማያወላዳ ይሆናል ያሉት ካትዝ በቀናት ውስጥ “ምናልባትም ነገ”ወደ ጦርነቱ ልንመለስ እንችላለን በሚል አሳስበዋል።
ከአሜሪካ ጋር እየተደራደረች ወደ እስራኤል ጥቃት የማድረስ ፍላጎት ኢራን አላት ብለዋል እስራኤል ካትዝ።
“ኢራን ጥቃት ካደረሰች፤ሶስተኛው የኢራን ጦርነት ይሆናል፤ነገሩ እጅግ ግልፅም ነው”በሚል አፅንዖት ሰጥተዋል።
እስራኤል ሚሳዔል ሲወነጨፍባት አደገኛ ምላሽ ሳትሰጥ አታልፈውም የሚል መረጃም ሚኒስትሩ አጋርተዋል።
በኢራን ላይ ያለማንም ደጋፊ  ፣ራሳችንን ችለን ጥቃት ለማድረስ እንዲሁም ሰማያዊ እና ነጭ ዘመቻ(ብሉ ኤንድ ዋይት) ኢራን ውስጥ ለማድረግ ጦሩ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ ብለዋል።
ብሉ ኤንድ ዋይት ዘመቻ በእስራኤል ጦርና ፖለቲከኞች ራስን ችሎ ማጥቃት የሚል ትርጓሜ ይሰጠዋል መባሉን ፎክስ ኒውስን ጠቅሰው ኤን ቢሲ ዘግቧል ።

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2