#Ethiopia | የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በ607 የፈተና ማዕከላት በስድስት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።
ለፈተናው በድምሩ 563,501 ተፈታኞች የተመዘገቡ ሲሆን፣ 306,456 የተፈጥሮ ሳይንስ እና 257,045 የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ናቸው።
አገልግሎቱ ለፈተናው የሚያስፈልጉ ሁሉንም ዝግጅቶች ማጠናቀቁንና የፈተና አስፈጻሚዎችን ወደ ፈተና ማዕከላት ማሰማራቱን ገልጿል።
ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከላት ሲቀርቡ የመፈተኛ መግቢያ ካርዳቸውን (Admission Card)፣ የተማሪ ወይም ህጋዊ መታወቂያ፣ በፈተና አስተዳደሩ የተፈቀደ እስክሪብቶ እና ባዶ ወረቀት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
ሞባይል ስልክ፣ ስማርት ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ጆሮ ማዳመጫ፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ሜሞሪ ካርድ፣ የግል ላፕቶፕ ወይም ታብሌት እና ሌሎች ያልተፈቀዱ መሳሪያዎችን ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት አይፈቀድም።
ፈተናው በበይነ መረብ በ6 ዙር የሚሰጥ ሲሆን፣ በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 1 እስከ 3፣ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ከሐምሌ 6 እስከ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚፈተኑ ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ተፈታኞች መልካም እድል እየተመኘ፣ ፈተናውን በመረጋጋት፣ በሥነ ምግባር እና በራስ መተማመን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።
Credit : EAES
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.