“የሕወሃት አመራር ወደ አዲስ አበባም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ የመጓዝ ፍላጎት የለውም!” -ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር
የፌዴራል መንግሥቱ በአሁኑ ወቅት ወታደሮቹን ከምዕራብ ትግራይ ወደ ምስራቅ ትግራይ እያሠማራ መሆኑን የሕወሃት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር በዛሬው ማምሻ ጋዜጣዊ መግለጫቸው አስታውቀዋል። በትግራይ ቴሌቪዥን በተላለፈው በዚህ መግለጫ ላይ ኃላፊዋ አሜሪካ በ”አክራሪ” የሕወሃት አመራሮችና አባላት ላይ የጣለችውን የቪዛ እገዳ አስመልክተው የተናገሩ ሲሆን፥ እገዳው በግለሰቦች ላይ ሳይሆን በሕወሃት “መርሆች” ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ ሕወሃት በመሠረታዊ መርሆዎቹ ላይ ፈጽሞ እንደማይደራደር አጽንዖት ሰጥተዋል።
ፈትለወርቅ አክለውም፥ የሕወሃት አመራር ወደ አዲስ አበባም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ የመጓዝ ፍላጎት እንደሌለው ለአሜሪካ ማሳወቃቸውን ገልጸዋል። የትግራይ ሕዝብና የድርጅቱ ጥያቄ ራስን በራስ የማስተዳደርና የራስን ዕጣ ፈንታ በራስ የመወሰን መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊዋ፥ የአሜሪካ ጥቅም ሊረጋገጥ የሚችለው ሕወሃትን በማስፈራራት ሳይሆን አብሮ በመስራት ብቻ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.