#FastMereja I በሰሜን ሸዋ ዞን የፊቼ ከተማ አስተዳደር፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ በመልበስ እና የጦር መሳሪያ በመያዝ የዘረፋ ወንጀል ስትፈጽም የነበረች ሴት በቁጥጥር ስር ዋለች።
ተጠርጣሪዋ አበባ ቁንቢ ትባላለች። የፊቼ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምክትል ኢንስፔክተር ቶልቻ ኃይሉ ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ ተጠርጣሪዋ የፖሊስ የደንብ ልብስ በመልበስ እና ሽጉጥ በመታጠቅ የተለያዩ የዘረፋ ወንጀሎችን ስትፈጽም ቆይታለች።
በተለያዩ የንግድ ተቋማት በመሄድ የዞን ፖሊስ መምሪያ አባል ነኝ ገንዘብ ረስቼ ወጥቼ ነው በማለት የምትፈልገውን ከሱቅ ትወስዳለች።
እምነት ለማትረፍ ስትል የራሷን ፎቶ እና ሽጉጥ ታጥቃ የተነሳችውን ምስል በማሳየት እቃዎችንና አልባሳትን በግድ ትወስድ እንደነበር ፖሊስ አስታውቋል።
በሌላ በኩል፣ ሌሊትን በመጠቀም ከሌሎች ተባባሪዎቿ ጋር በመሆን ሰዎችን በጦር መሳሪያ በማስፈራራት ስትዘርፍ እንደነበር ምርመራው አረጋግጧል።
ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ፖሊስ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪዋን ተከራይታ በምትኖርበት ቤት ውስጥ ከአንድ የቱርክ ሽጉጥ፣ አንድ የወገብ ካርታ፣ሁለት የክላሽንኮቭ ጥይት ካርታ፣ አንድ ጎራዴ፣ ከተለያዩ የፖሊስ የደንብ ልብሶች እና ሶስት የፖሊስ ዱላዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተጣራባት እንደሚገኝና ለህግ እንደምትቀርብ የፊቼ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
#ችሎት
Source: FastMereja









No comments yet.