🇩🇪
ፓራጓይ በመለያ ምቶች አስደናቂ ድል ተቀዳጀች
#Ethiopia | አራት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን የሆነችው የጀርመን ቡድን በ2026 የዓለም ዋንጫ የ32 ቡድኖች ዙር ከፓራጓይ ጋር 1–1 አቻ ከተለያዩ 120 ደቂቃዎች በኋላ በመለያ ምቶች ተሸንፋ ከውድድሩ ተሰናብታለች።
ጨዋታው እጅግ ፉክክር የበዛበት ሲሆን፣ ጀርመን ብዙ የጎል ዕድሎችን ብታገኝም የፓራጓይን ጠንካራ መከላከል ማለፍ አልቻለችም። በተጨማሪ ሰዓት የተቆጠረ የጀርመን ጎል በVAR ከተሰረዘ በኋላ ጨዋታው ወደ መለያ ምቶች አምርቶ ፓራጓይ 4-3 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
ይህ ውጤት ለፓራጓይ ታሪካዊ ድል ሲሆን፣ ለጀርመን ደግሞ በዓለም ዋንጫ ታሪኳ የመጀመሪያው በመለያ ምቶች የደረሰባት ሽንፈት ሆኖ ተመዝግቧል።



Source: GetuTemesgen








No comments yet.