ሃሪ ኬን እንግሊዝን ታደገ፤ ሶስቱ አንበሶች ዲሞክራቲክ ኮንጎን አሸንፈው ወደ 16ቱ ተቀላቀሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የዲሞክራቲክ ኮንጎን አቻውን 2 ለ 1 በሆነ ጠባብ ውጤት በመርታት ወደ 16ቱ መግባቱን አረጋግጧል።

ጨዋታው እንደተጀመረ ብርቱ ፉክክር ያስመለከተ ሲሆን፣ የዲሞክራቲክ ኮንጎው “ብሪያን ሲፔንጋ” ገና በ7ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ቀደምት ግብ ኮንጎውያንን መሪ ማድረግ ችላ ነበር።

እንግሊዞች ግብ ከተቆጠረባቸው በኋላ የአቻነትን ግብ ለመፈለግ ከፍተኛ ጫና ፈጥረው ቢጫወቱም፣ የመጀመሪያው አጋማሽ በዲሞክራቲክ ኮንጎ 1 ለ 0 መሪነት ተጠናቋል።

በሁለተኛው አጋማሽ ተጭነው መጫወታቸውን የቀጠሉት እንግሊዞች፣ ጨዋታው ሊጠናቀቅ 15 ደቂቃዎች ሲቀሩት ነው የድል አቅጣጫቸውን የቀየሩት።

ድንቅ ብቃቱን ያሳየው አንጋፋው አጥቂ ሪ ኬን በ75ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን አቻ ሲያደርግ፣ ከአስር ደቂቃዎች በኋላ በ86ኛው ደቂቃ ላይ ሁለተኛዋንና ለአሸናፊነት ያበቃቻቸውን ወሳኝ ግብ ከመረብ አሳርፏል።

“ይህ ድል የቡድናችንን የአእምሮ ጥንካሬ ያሳየ ነው፤ ተስፋ ሳንቆርጥ እስከ መጨረሻው ተዋግተናል” — የእንግሊዝ ደጋፊዎች አስተያየት።

የቀጣይ ዙር ፈተና
ዲሞክራቲክ ኮንጎን ያሸነፈችው እንግሊዝ በቀጣዩ የ16ቱ ጥሎ ማለፍ ዙር ከውድድሩ አስተናጋጅ ሜክሲኮ ጋር የምትገናኝ ይሆናል።

ይህ ጨዋታ በደጋፊዎች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ ሲሆን፣ እንግሊዝ ከሜክሲኮ ብርቱ ፈተና እንደሚጠብቃት የስፖርት ተንታኞች እየገለጹ ይገኛሉ።


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1