የአዲስ አበባ ሯጮች በአፍሪካ እምብርት ላይ በሚካሄድ ማራቶን ላይ እንዲሳተፉ ግብዣ ቀረበ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢትዮዽያ ሩጫ ከስፖርት በላይ ነው ፤ ሩጫ የሀገር ኩራት፣ የጋራ በዓል፣ የጤና ፣ የህብረተሰብ ትስስር እና የነፍስ ደስታ ነው።

በአፍሪካ ዕምብርቷ ኡጋንዳም ተመሳሳይነት ያለውን ስሜት ለመጋራት፣ ታላቁ ሩጫ በኢትዮዽያ ከተስከር ላይት ሩዌንዞሪ ማራቶን ጋር በመተባበር ለሩጫ ወዳጆች ጥሪን አቅርቧል።

ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የምስራቅ አፍሪካን ተራራማ መልክዓ ምድር ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱን የሩጫ ውድድር ወደ ታላቅ በዓል የመቀየር ተመሳሳይ ባህል አላቸው። ከአዲስ አበባ ለሚሄዱ ሯጮች በካሴሴ የሚስተዋለው የባህል ድባብ፣ ሙዚቃ እና የህዝብ አቀባበል እንደ ቤት እንዲሰማ የሚያደርግ የቅርብነት ስሜት አለው።

በሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ፣ በእንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ ላይ የሚሳተፉ እና ሌሎችም የሩጫ አፍቃሪያን፣ ያንኑ የሩጫ መንፈስ በመያዝ ከሀገር ውጪ በመጓዝ ውድድሩን እንዲቀላቀሉ እንጋብዛለን።

ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. በኡጋንዳ፣ ካሴሴ ከተማ የሚካሄደው ተስከር ላይት ሩዌንዞሪ ማራቶን፣ ከአዲስ አበባ የባህር ዛፍ ጠረን ካለው ቀዝቃዛ አየር ወደ ሳቫናው ግርማ ሞገስ እና ወደ ሩዌንዞሪ ተራሮች ግርጌ የሚያደርጉት ልዩ የሩጫ ጉዞ ነው። በኢትዮጵያ የክረምቱ ዝናብና ቅዝቃዜ ሲጠነከር፣ በዩጋንዳ ካሴሴ ደግሞ ሞቅ ያለ ፀሐይና የኢኩዌተር መስመር ላይ የሚደረግ ውድድር ይጠብቅዎታል።

የተስከር ላይት ሩዌንዞሪ ማራቶን የዓለም አትሌቲክስ ሌብል (World Athletics Label Road Race) ደረጃ ያለዉ ዉድድር ነዉ። ይህም በአትሌቶች ጥራት እና በአደረጃጀት በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ 200 ውድድሮች አንዱ ያደርገዋል። በውድድሩ ከማራቶን በተጨማሪ በ5 ኪ.ሜ.፣ 10 ኪ.ሜ.፣ እና 21 ኪ.ሜ . (ግማሽ ማራቶን) መሳተፍ ይችላሉ።

የሩጫው መስመር በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ በሆነው የንግስት ኤልሳቤጥ ብሔራዊ ፓርክ ይጀምራል። በከበሮና በሙዚቃ በምትደምቀው የካሴሴ ከተማ መንገዶች አድርጎ፣ በበረዶ በተሸፈኑት የሩዌንዞሪ ተራሮች ግርጌ በሚገኘው አስደናቂው የኪሌምቤ ሸለቆ ይዘልቃል። ማጠናቀቂያው ላይ ሲደርሱ፣ ከኋላዎ የተዘረጋው ግዙፍ የተራራ ሰንሰለት ለእርስዎ የሚሰጠው ስሜት ምን ያህል ድንቅ እንደሆነ በራስዎ ይመሰክራሉ።

እንዴት መመዝገብ ይቻላል?

ይህንን ታላቅ የሩጫ በዓል ለመቀላቀል እና በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ፣ አሁኑኑ ከዚህ በታች በተቀመጠው ድረ-ገጽ አማካኝነት በመግባት መመዝገብ ይችላሉ።

www.rwenzorimarathon.com/register






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2