የሊቢያው ኦላ ኢነርጂ የቶታልኤነርጂስን የኢትዮጵያ ንብረቶች በሙሉ ጠቀለለ
የሊቢያው ኦላ ኢነርጂ ግሩፕ በኢትዮጵያ የሚገኙትን የፈረንሳዩ ቶታልኤነርጂስ ንብረቶች በሙሉ ለመጠቅለል የሚያስችለውን የግዢ ስምምነት በፓሪስ ተፈራረመ።
ይህ ስምምነት ኦላ ኢነርጂ በኢትዮጵያ የነዳጅ ማከፋፈል ገበያ ውስጥ ትልቁ የውጭ ኩባንያ ያደርገዋል።
ይህ ግዙፍ የአክሲዮን ግዢ በኢትዮጵያ የሚገኙ ወደ 120 የሚጠጉ የነዳጅ ማደያዎችን፣ የ13 ሺህ ሜትር ኩብ አቅም ያለውን የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል እና ተያያዥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ያጠቃልላል።
በስምምነቱ ላይ የሊቢያ ዘይትና ጋዝ ሚኒስትር ከሊፋ አብዱልሳዲቅ እና የቶታልኤነርጂስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓትሪክ ፑያን ጨምሮ የሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ግዢው ሊቢያ በአፍሪካ አህጉር ያላትን የኢኮኖሚ ተፅዕኖ እና የውጭ ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት የምታደርገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.