ጃምቦ ሪል እስቴት ከፋስት ፔይ ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራረመ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤቶች ልማት ዘርፍ የሚንቀሳቀሰው ጃምቦ ሪል እስቴት፣ የደንበኞቹን የክፍያ አማራጮች ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ ለማድረግ ከፋስት ፔይ ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራርሟል።

ስምምነቱ በተለይም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከጃምቦ ሪል እስቴት የሚገዙትን መኖሪያ ቤቶች ክፍያ በአስተማማኝና በቀላል መንገድ እንዲፈጽሙ ለማስቻል የታለመ መሆኑ ተገልጿል።

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደተገለጸው፣ ፋስት ፔይ በኢትዮጵያና በአሜሪካ ሕጋዊ ዕውቅና ያለው የፋይናንስ ቴክኖሎጂ (ፊንቴክ) ተቋም ሲሆን፣ በዲጂታል የክፍያ መፍትሔዎች ላይ የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣል።

የጃምቦ ሪል እስቴት ተወካዮች በዝግጅቱ ላይ እንደገለጹት፣ አጋርነቱ የድርጅቱን የክፍያ ሥርዓት ይበልጥ ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል።

በሌላ በኩል፣ የፋስት ፔይ መሥራችና የቴክኖሎጂ ኃላፊ አቶ ሞቱማ በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት፣ ስምምነቱ በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ዲያስፖራዎች ለቤት ግዢ የሚያደርጉትን ክፍያ የበለጠ አስተማማኝና ምቹ እንደሚያደርግ ገልጸው፣ በቀጣይም ከጃምቦ ሪል እስቴት ጋር በተለያዩ ዘርፎች የጋራ ሥራዎችን እንደሚያከናውኑ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ጃምቦ ሪል እስቴት በሰሜን አሜሪካ በሚካሄደው የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌስቲቫል የ”ነሐስ” ደረጃ ስፖንሰር መሆኑንም አስታውቋል።





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1