ገዳ ባንክ በበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት 1 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ
👉 ካለፈዉ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ113 በመቶ ብልጫ አሷይቷል
የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ወልዴ ቡልቶ በትናንትናዉ ዕለት በሰጡት መግለጫ ባንኩ አዲስ ዘመናዊ ዋና መስሪያ ቤት ለመገንባት የመጀመሪያዉን ምዕራፍ አጠናቆ የህንፃዉን ዲዛይንና ግንባታ ለማስጀመር በጨረታ ላይ መሆኑን መናገራቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሠምቷል ።
ባንኩ ከተመሠረተ አጭር ዓመት ያስመዘገበ ቢሆንም በበጀት ዓመቱ ሁለንተናዊ እድገት ማስመዝገቡ የተገለፀ ሲሆን የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 16.5 ቢሊዮን ብር መድረሱንና ይህም ከቀዳሚዉ ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ64 በመቶ ብልጫ እንዳለዉ ተገልጿል ።
የባንኩ ተቀማጭ ሂሳብ 12 ቢሊዮን ብር መድረሱ የተነገረ ሲሆን የባንኩ ገቢ ከ2.9 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ እና ይህም የ82 በመቶ እድገት እንዳለዉ ተመላክቷል ።
ገዳ ባንኩ በአሁኑ ወቅት የቅርንጫፎቹን ቁጥር 113 ማድረስ የቻለ ሲሆን የዲጂታል ባንኪንግ እና ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን በስፋት ለደንበኞቹ ተደራሽ ማድረግ መቻሉ ተጠቁሟል ።
ባንኩ የአክሲዮን ሽያጭ ለማከናወን ማቀዱንና የአንድ አክሲዮን ዋጋ 1ሺህ 50 ብር መሆኑን አስታውቋል ።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.