ለ38 ዓመታት በስዊዲን ኤምባሲ ያገለገሉት አስካለ አበበ በክብር ተሸኙ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በኢትዮጵያ የስዊድን ኤምባሲ ውስጥ ላለፉት 38 ዓመታት በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ በታማኝነት እና በትጋት ሲያገለግሉ የቆዩት አንጋፋዋ ሰራተኛ ወይዘሮ አስካለ አበበ በክብር ስራቸውን አጠናቀው ጡረታ መውጣታቸውን ኤምባሲው አስታውቋል።

​ለአራት አስርት ዓመታት ገደማ በዘለቀው የአገልግሎት ዘመናቸው በርካታ አምባሳደሮችን፣ የዲፕሎማቲክ ቡድኖችን እና እንግዶችን በደገፉት ወይዘሮ አስካለ አበበ አሸኛኘት ላይ በቪዲዮ መልዕክት ጭምር ምስጋና የቀረበላቸው ሲሆን፣ የኤምባሲው የስራ ባልደረቦችም በቆይታቸው ላበረከቱት አስተዋጽዖ ያላቸውን አክብሮት ገልጸውላቸዋል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1