ኡጋንዳ የተዘጋጀ የሥጋ ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ መላክ ጀመረች
ሬንቸርስ ፋይነስት (Ranchers Finest Ltd) የተባለው የኡጋንዳ ሥጋ አቀነባባሪ ኩባንያ የመጀመሪያውን ዙር የተዘጋጁ የሥጋ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ መላኩን አብስሯል።
በዚህም በሁለቱ አገራት የአግሮ-ቢዝነስ ዘርፍ አዲስ የንግድ ምዕራፍ መጀመሩ ተመላክቷል።
ይህ ምርት በኢትዮጵያ ለሚገኘው «ዳይመንድ ሆቴል እና ሬስቶራንት ግሩፕ» (Diamond Hotel and Restaurant Group) የሚቀርብ ሲሆን፣ በስምምነቱ መሠረት ኩባንያው በየወሩ 20 ቶን የሚጠጋ የሥጋ ምርት ያቀርባል።
ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩት የሥጋ ምርቶች፦
* የበሬ ሥጋ ቁርጮች (Beef cuts)
* ሶሴጅ (Sausages)
* ስቴክ (Steaks)
* የበግ ሥጋ ምርቶች (Lamb products)
የኡጋንዳ ባለሥልጣናት እንደገለጹት፤ ይህ ንግድ አገሪቱ ጥሬ የቀጥታ ከብቶችን ከመላክ ወጥታ እሴት የተጨመረባቸውና ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኙ የተዘጋጁ የሥጋ ምርቶች ላይ ትኩረት ማድረጓን የሚያሳይ ትልቅ ስኬት ነው።
ንግዱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ያጠናክረዋል ተብሏል።
ምርቱ በየወሩ በተከታታይ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ይቀጥላል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.