በትግራይ ወጣቶች እየታፈሱ መሆኑ ተሰማ በትግራይ ክልል ወጣቶች ላይ እየተፈጸመ ስላለው እፈሳ በርካታ የጉርሻ ፔጅ ተከታታዮች በ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በትግራይ ወጣቶች እየታፈሱ መሆኑ ተሰማ
በትግራይ ክልል ወጣቶች ላይ እየተፈጸመ ስላለው እፈሳ በርካታ የጉርሻ ፔጅ ተከታታዮች በከፍተኛ ስጋት ጥቆማዎችን እያጋሩን ይገኛል።
ጉርሻ ፔጅ ነገሩን ይበልጥ ለማጣራት ባደረገው ቆይታ፣ ከትምህርት ቤት እየተመለሱ ያሉ ወጣቶች በኃይል እየተወሰዱ መሆናቸውን ስማቸውን መግለጽ የማይፈልጉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸውልናል።
ዛሬ በመቀሌ ቀበሌ 06 ከትምህርት ቤት አካባቢ በተቀረጸና ለእኛ በደረሰን የቪዲዮ ማስረጃ ላይ እናቶች መሬት እያመቱ በከፍተኛ ጩኸትና ኃዘን ሲያለቅሱ ይታያል።
ጉርሻ ፔጅ ከድሮም ጀምሮ በእርስ በእርስ ጦርነት የማያምን፣ እንዲሁም ከዚህ ቀደም በተካሄደው ጦርነት ላይ እጁን ያላስገባ ሰላማዊ መድረክ መሆኑ ይታወቃል።
የትግራይ ወጣቶች እንደማንኛውም ክልል ያሉ ወጣቶች የመስራት፣ የመለወጥና የማደግ ትልቅ እሳቤና ህልም ያላቸው በመሆኑ ይህ የወደፊት ተስፋቸው ሊቀጭ አይገባም ብለን እናምናለን።
ስለሆነም የሚመለከተው የክልሉ አካልም ሆነ የፌዴራል መንግስቱ ይህንን ነገር በአስቸኳይ እንዲያስቆመው በትህትና እንጠይቃለን።
ጠግበህ በልተህ እንኳን የበላህ የማይመስላት የትግራይ እናት አደይ አሁን ማልቀስ የለባትም። gursha
@Seledadotio
@Seledadotio


Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2