#Ethiopia | የቲኬ ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ እንዲሁም የ2018 ዓ.ም. የ”ምርጥ የአፍሪካ ኢንቨስተር” ልዩ የዳይመንድ ሽልማት አሸናፊ የሆኑት የክብር ሼህ ቶፊቅ ከድር፣ የኢትዮጵያ ዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል።
ሼህ ቶፊቅ በሰኔ ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያ ሆቴል በተካሄደው የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በአባላቱ ሙሉ እምነት ለዚህ ከፍተኛ ኃላፊነት ተመርጠዋል።
በቡልቡላ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ባቋቋሟቸው ሰባት ፋብሪካዎች የምግብ ዘይት፣ ስጋ ተኪ ፕሮቲን ምርቶች እና የእንስሳት መኖዎችን በከፍተኛ ጥራት በማምረት እንዲሁም በማህበራዊ ኃላፊነት ሥራዎቻቸው ባስመዘገቡት ውጤት ለዚህ ኃላፊነት በቅተዋል።
ከዚህ ቀደምም በኢንዱስትሪው ዘርፍ ላሳዩት የላቀ አመራር፣ ፈጠራ፣ ራዕይ እና ለዘርፉ እድገት ላበረከቱት አስተዋጽኦ “Diploma of Leadership Excellence” በተሰኘ ልዩ የአመራር ዲፕሎማ ተሸልመዋል።
በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ የላቀ የንግድና የኢንዱስትሪ አፈጻጸም ያስመዘገቡት ሼህ ቶፊቅ ከድር ሲራጅ፣ በአዲሱ የፕሬዚዳንትነት ኃላፊነታቸው የኢትዮጵያን የዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች ተግዳሮቶች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ወደ መፍትሔ እንደሚያመጡ ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።
ሥራን በውጤት ያረጋገጠ አመራር ወደ ትልቅ ኃላፊነት ሲመጣ ለዘርፉም ሆነ ለሀገር እድገት ተስፋ የሚሰጥ ነው።
እንኳን ደስ አላችሁ!
Source: GetuTemesgen








No comments yet.