ፈረንሳይ ፓራጓይን አሸንፋ ወደ ሩብ ፍጻሜ አለፈች፤

- Advertisement -
Sidebar AD

* የአፍሪካ ተወካዮች በመጨረሻ ደቂቃዎች ተሰናበቱ

#Ethiopia | በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የ16 ቡድኖች ጥሎ ማለፍ ዙር ፈረንሳይ ፓራጓይን 1 ለ0 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ አልፋለች።

የጨዋታውን ብቸኛ ግብ በ70ኛው ደቂቃ ኪሊያን ምባፔ ከፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።

በሩብ ፍጻሜውም ፈረንሳይ ከሞሮኮ ጋር ትፋለማለች።

በሌላ በኩል የአፍሪካ ተወካዮች ታሪካዊ ውጤት ለማስመዝገብ በጣም ተቃርበው ቢደርሱም በመጨረሻ ደቂቃዎች ልፋታቸው ሳይሳካ ቀርቷል።

ደቡብ አፍሪካ በ91ኛው ደቂቃ፣

ኮትዲቯር በ87ኛው ደቂቃ፣

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በ86ኛው ደቂቃ

እንዲሁም ኬፕ ቨርዴ በ111ኛው ደቂቃ ከውድድሩ ተሰናብተዋል።

ሴኔጋልም እስከ ተጨማሪ ሰዓት 120ኛው ደቂቃ ድረስ ተፋልማ በመጨረሻ ከውድድሩ ተሰናብታለች።

የእነዚህ ቡድኖች መሰናበት የአፍሪካ እግር ኳስ ደጋፊዎችን እጅግ አሳዝኗል፤ ቡድኖቹ ታሪክ ለመጻፍ በጣም ተቃርበው ቢደርሱም በመጨረሻ ደቂቃዎች የውድድሩን ጨካኝ ተፈጥሮ በድጋሚ ተጋፍጠዋል።




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: