#Ethiopia | የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ደረጀ ድጉማ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከኬንያ የሕዝብ ጤና እና ሙያዊ ደረጃዎች መምሪያ ዋና ጸሐፊ ሜሪ ሙቶኒ ጋር የምክክር ስብሰባ አካሄዱ።
የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ ኬንያ የእናቶችና ሕፃናትን ጤና ለማሻሻል በሰው ሰራሽ አስተዋጽኦ (AI) የታገዘ አልትራሳውንድ ቴክኖሎጂን (AI-POCUS) በመተግበር ረገድ ያካበተችውን ተሞክሮ ለኢትዮጵያ ማጋራት ነው።
በስብሰባው ወቅት ኬንያ በዲጂታል ጤና ፈጠራ፣ በመልካም አስተዳደር እና የኤአይ አልትራሳውንድ አገልግሎትን በማስፋፋት ረገድ ያስመዘገበችው እድገት የቀረበ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂን በሀገር ውስጥ በመዘርጋት የእናቶችና ሕፃናትን ሕክምና ለማጠናከር ለምናደርገው ዝግጅት ትልቅ ጥቆማ የሚሰጥ ነው ተብሏል።
ይህ ውይይት ኢትዮጵያና ኬንያ በዲጂታል ጤና መፍትሔዎች፣ በእውቀት ሽግግር እና በቀጣናው ጠንካራ የጤና ስርዓት በመገንባት የእናቶችና ሕፃናትን የጤና ሁኔታ ለማሻሻል ያላቸውን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም ያረጋገጡበት ሆኖ አልፏል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.