የፓኪስታን ጦር ቀይ ባህር ደጃፍ ተጠግቷል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ይህ አዲስ ወታደራዊ ጥምረት በሕንድ ውቅያኖስ እና በቀይ ባሕር አካባቢ ባሉ ሀገራት ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት እና ውጥረት አሳድሮባቸዋል።

በሕንድ ውቅያኖስ እና በዓለም አቀፉ የንግድ መርከቦች ዋና ማለፊያ በር ላይ ከፍተኛ የጂኦፖለቲካ ውጥረት የሚቀሰቅስ አዲስ ወታደራዊ ጥምረት ተመሰረተ።

ፓኪስታን እና ሶማሊያ በሽብርተኝነት መከላከ በስልታዊ ወታደራዊ ስልጠና እና በዘመናዊ የደህንነት አቅም ግንባታ ላይ ያተኮረ ስምምነት አድርገዋል።

ይህ ስምምነት እስላማባድ በዓለም ንግድ ላይ ቁልፍ በሆነው ባቢ ኤል ማንደብ እና በሕንድ ውቅያኖስ ላይ ያላትን የጦር እና የደህንነት ተፅዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያጠነክር ነው ተብሏል።

በስምምነቱ መሰረት የባሕር ላይ ውንበዴዎች እና የሽብርተኛ ድርጅቶች እንቅስቃሴ በጋራ መታገል እንዲሁም የሶማሊያን ጦር ኃይል በዘመናዊ መንገድ ማደራጀት የትብብሩ ዋና አካል ናቸው።

የፓኪስታን ጦር ወደ ቀይ ባሕር ደጃፍ መጠጋት በምስራቅ አፍሪካ እና በገልፍ ሀገራት መካከል ያለውን የኃይል ሚዛን አዲስ መልክ ሊያሲዝው እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ተናግረዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Pakistan #Somalia
#Defence #agreement
#geopolitical #trade


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: