ራሽፎርድ ልምምድ ሰርቷል ቀጣይስ?

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ማርከስ ራሽፎርድ ወደ ካሪንግተን ከተመለሰ በኋላ በካሪንግተን የመጀመርያ ልምምዱን ሰርቷል።

ተጫዋቹ ከማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ጋርም ፎቶ ተነስቷል።

የማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ ዛሬ በካሪንግተን የስልጠና ማዕከል በመገኘት ወደ ልምምድ ተመልሷል።

ተጫዋቹ በማዕከሉ ደጃፍ ከተሰበሰቡ የክለቡ ደጋፊዎች ጋር ፎቶግራፍ በመነሳትና ፊርማ በመፈረም ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎለታል።

በባርሴሎና በውሰት ያሳለፈው ቆይታ ከተጠናቀቀ በኋላ ባርሳ በቋሚነት የመግዛት አማራጩን ባለመጠቀሙ ወደ ማንቼስተር ዩናይትድ ተመልሷል።

ካሪክ እንዳረጋገጠው ራሽፎርድ ከኮቢ ማይኑ እና ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ጋር በመሆን ቡድኑ ወደ አየርላንድ ለሚያደርገው የቅድመ ውድድር ዘመን ስልጠና ካምፕ አብሮ ተጉዟል ብሏል።

አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ተጫዋቹን በ2026/27 የውድድር ዘመን በዩናይትድ ቆይቶ እንዲጫወት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Manchesterunited
#MarcusRashford


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1