#Ethiopia | የስፔን መንግሥት ጣሊያን የወሰደችው ውሳኔ የአውሮፓ ህብረት የሼንገን መርህና ስምምነት የሚጥስ ነው በሚል ከሷል።
በስፔኗ የሰሜን አፍሪካ ግዛት ሰኡታ አቅራቢያ አጋጥሞ የነበረውን ከፍተኛ የስደተኞች ፍሰት ተከትሎ ጣሊያን ከስፔን በሚመጡ የአየር እና የባህር መንገደኞች ላይ የጣለችውን ጊዜያዊ ቁጥጥር ይቀጥላል ብላለች።
ስፔን የአጸፋ እርምጃ እወስዳለሁ ብላ ብታስፈራራም ጣሊያን ቁጥጥሩ እንደምትቀጥልበት አስታውቃለች።
በቅርቡ ከ60,000 በላይ የሚሆኑ ህገ ወጥ ስደተኞች ከሞሮኮ ወደ ስፔኗ ሰኡታ መግባታቸውን ይታወሳል።
የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የአውሮፓ ሼንገን ስምምነትን በጊዜያዊነት በማገድ ከስፔን ወደ ጣሊያን በሚገቡ መንገደኞች ላይ ቁጥጥር እንዲደረግ ወስነዋል።
የስፔን መንግሥት የጣሊያን ውሳኔ የሼንገን መርህና ስምምነት የሚጥስ ነው በሚል ከሳለች።
ጣሊያን የስፔን ዜጎችን እንደ ሌሎች የአውሮፓ ሕብረት ሀገራት ዜጎች የማታስተናግድ ከሆነ ተመሳሳይ የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ ስፔን ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።
የጣሊያን ባለስልጣናት በበኩላቸው እርምጃው የሀገሪቱን የውስጥ ደህንነት ለመጠበቅና ቁጥጥር የሌለው የስደተኞች እንቅስቃሴ ወደ ሌሎች አውሮፓ ሀገራት እንዳይስፋፋ ለመከላከል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#EuropeanUnion
#Spain #Italy #migration
Source: GetuTemesgen









No comments yet.