በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ባለፈው ሰኞ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አባላት አቶ አበበ አካሉ እና አቶ ይስሀቅ ወልዳይ እንዲሁም የፓርቲው ጠበቃ አቶ አበራ ንጉስ ላይ ፍርድ ቤት የ12 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።
የምርመራ ጊዜውን የፈቀደው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ፣ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። ችሎቱ ለዛሬ ቀጥሮ ተጠርጣሪዎች ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነበር።
ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ከማስተላለፉ አስቀድሞ፤ ፖሊስ በጊዜ ቀጠሮ ማመልከቻው ያካተተውን እና ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ጋር ያደረጓቸውን ቃለ ምልልሶች ሊንኮች በትላንትናው ዕለት እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል።
የፌደራል ፖሊስ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ማመልከቻ ላይ ተጠርጣሪዎቹ “የብሔር እና የሃይማኖት ግጭትን ለመፍጠር በማሰብ በውጭ ሀገር በሚገኙ መገናኛ ብዙኃን ሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ነበር” የሚል ውንጀላ አቅርቦ ነበር።
ከመገናኛ ብዙሃኑ መካከል በፖሊስ ማመልከቻ ላይ በስም የተጠቀሱት አንከር ሚዲያ፣ ኢትዮ ፎረም እና ኢትዮ 360 መገናኛ ብዙሃን ናቸው።
ከመገናኛ ብዙሃን ጋር የተደረጉ ቃለ ምልልሶችን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት፤ ፖሊስ ሊንኮቹን ለችሎቱ ማቅረቡን የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ጋር አድርገዋቸዋል የተባሉትን ቃለ ምልልሶች ያደመጠው ፍርድ ቤቱ፤ ንግግሮቹ በሽብር ወንጀል ለመጠርጠር “መነሻ ይሆናሉ” ማለቱን አቶ ሰለሞን አስረድተዋል።

No comments yet.