#Ethiopia | በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች በስኬት እየደመቀች የምትገኘው ታዳጊ አትሌት አልማዝ ዮሐንስ ስሟ በዓለም እየናኘ ነው።
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ውስጥ ተስፋ ሰጪ ከሆኑ አዳዲስ ተካኪ ስፖርተኞች መካከል አንዷ የሆነችው አትሌት አልማዝ ዮሐንስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ስኬት በማስመዝገብ ላይ ትገኛለች።
በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በዓለም አቀፍ እና በአህጉራዊ ውድድሮች ሁለት ሜዳሊያዎችን ለሀገሯ ማስገኘት የቻለችው ይህች ታዳጊ አትሌት፣ የስፖርት አፍቃሪዎችን ትኩረት ስባለች።
በሲዳማ ክልል አርቤጎና ወረዳ ከሮ ጫንጮ ቀበሌ የተወለደችው የ19 ዓመቷ አልማዝ ዮሐንስ፣ የስፖርት ጉዞዋን የጀመረችው በአርቤጎና ታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት ውስጥ ነበር።
በስፖርቱ ያላትን ከፍተኛ ፍላጎት፣ የውስጥ ጥንካሬ እና ድፍረት በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ እድገት በማሳየት ወደ ሲዳማ ቡና አትሌቲክስ ክለብ ተቀላቅላለች። በሀገር ውስጥ በተካሄዱ ውድድሮችም የላቀ ብቃት በማሳየት የክለቧን ስም ማስጠራት ችላለች።
በሀገር ውስጥ ያሳየችውን ድንቅ ብቃት ተከትሎ ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ የተሸጋገረችው አትሌቷ፣ እ.ኤ.አ. በ2026 በፎሎሪዳ በተካሄደው የ6 ኪሎ ሜትር የሀገር አቋራጭ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን እንድትወክል ተመርጣ አስፈላጊውን ዝግጅት በብቃት ያጠናቀቀች ቢሆንም፣ በቪዛ ምክንያት በውድድሩ ላይ ሳትሳተፍ ቀርታለች።
ይሁን እንጂ በዚህ ሳትበገር ጥንካሬዋን በመቀጠል፣ በ2026 በጋና በተካሄደው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ3000 ሜትር መሠናክል ውድድር ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የነሐስ ሜዳሊያ ማሸነፍ ችላለች።
በአጭር ጊዜ ውስጥ ያስመዘገበችው ይህ ውጤት ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሩህ ተስፋ ያለው አዲስ ትውልድ እየተተካ መሆኑን ያሳያል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#almazyohannes #ethiopianathletics #sportsnews #athletics #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Source: GetuTemesgen









No comments yet.