አንድ ታላቅ የጥበብ ሰው እናስተዋውቃችሁ፤ መምህር፣ ደራሲ፣ ፀሐፊ፣ ዳይሬክተር እና ተዋናይ አታኽልቲ ነጋ፤ በትግራይ የፊልምና

- Advertisement -
Sidebar AD

አንድ ታላቅ የጥበብ ሰው እናስተዋውቃችሁ፤ መምህር፣ ደራሲ፣ ፀሐፊ፣ ዳይሬክተር እና ተዋናይ አታኽልቲ ነጋ፤ በትግራይ የፊልምና ድራማ ዘርፍ እንዲሁም በትግርኛ ቋንቋ እድገት ላይ የማይደበዝዝ አሻራ ያሳረፈ የጥበብ ዓምድ ነው። በጥንካሬና በትጋት የተገነባውን የጥበብ ህይወቱን በአድናቆት ስንቃኝ፤ ከሦስት አስርተ ዓመታት በላይ የዘለቀውን ጥበባዊ ውበቱንና ለትውልድ የተሻገረውን የጥበብ ፍቅሩን ስናስብ “ያለ ግንድ ቅርንጫፍ የለም” የሚለው የሊቃውንት አባባል በሚገባ ይገልጸዋል።

አታኽልቲ በልዩ የጥበብ ተሰጥኦ የታደለ፣ በብዕሩ ዓለምን የመዘነና ተመልካቹን ያስደመመ ብቻ ሳይሆን፤ ለኋለኛ የጥበብ መሪዎች ፈር ቀዳጅ በመሆን ያሳደገ እና ክብር ያጎናጸፈ ባለሙያ ነው። ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በነበረው የጥበብ ጉዞው፤ ከ20 በላይ ተከታታይ የቴሌቪዥን ኮሜዲዎችን እና 30 የሚሆኑ የሬዲዮ ድራማዎችን በማዘጋጀት ህዝብን ያስተማረና ያዝናና ስሙር ከዋክብት ነው።

“ማሾ” በተሰኘው ድንቅ ስራው በትግርኛ ፊልም ታሪክ ውስጥ ወርቃማ ምዕራፍ የጻፈው አታኽልቲ፤ በ”ምትሓታዊ ዓለባ” (ብርሆን ገይፀን) አማካኝነት በተመልካቾች ልብ ውስጥ ለዓመታት ነግሶ ይገኛል። ስራዎቹ በጥራትና በብቃት የተሞሉ በመሆናቸው፤ በሀገርና በክልል ደረጃ በተዘጋጁ ውድድሮች ምርጥ ደራሲ፣ ዳይሬክተር እና ተዋናይ በመሆን ተደጋጋሚ ተሸላሚ ሆኗል። ከ”ኣልሻ መንነት” እስከ “ሕርፍርፎት” ያሉ ስራዎቹ ባህልንና የማህበረሰቡን ለዛ የሚያንጸባርቁ የጥበብ መስታወቶች ናቸው።

ይህ ለጥበብ የተፈጠረ የጥበብ መምህር አሁንም ከፊልም ኢንዱስትሪው አልራቀም። የድምፁን ብርታት፣ የገለጻውን ፍሰትና የስራዎቹን ጣዕም ዳግም የምናይበት አዲስ ስራ ይዞ ቀርቧል። “ውሽጥን ደገን” (Inside/Outside) በተሰኘ አዲስ የሲትኮም ድራማ ያንን የተለመደ ጣፋጭ ጥበቡን ይዞ ተመልሷል።

ይህ “ውሽጥን ደገን” (Inside/Outside) የተሰኘው አዲስ ስራው፤ እሁድ ከሰዓት በኋላ በ8፡00 ሰዓት በመቀሌ ሰማዕታት ሐውልት በሚገኘው ሲኒማ አዳራሽ በደመቀ ስነ-ስርዓት የሚመረቅ መሆኑን እንገልጻለን። በዚህ የምረቃ ስነስርዓት ላይ ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ሁሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ለረጅም ጊዜ የተዘጋጀው ይህ ትልቅ ፕሮጀክት፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ በትግራይ ቴሌቪዥን በሳምንት ሦስት ጊዜ ለተመልካቾች እንደሚደርስ በደስታ እናበስራለን።

የአታኽልቲ ነጋ ክብር ከከበሩ ስራዎቹ በላይ እንደሆነ ይሰማናል። ይህንን የጥበብ ጀግና አዲስ ስራ “ውሽጥን ደገን” (Inside/Outside) በመደገፍና በመመልከት ፍቅራችሁን እንድትገልጹለት በአክብሮት እንጋብዛለን።

👉 ብቸኛ አዘጋጅ ( Exclusive producer ) ሸባ ኢንተርተይመንት
በክብሮም ገ/መስቀል

የዚህን ተከታታይ ድራማ ማስተዋወቂያ (Trailer) ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://youtu.be/T6zFaqse64o



Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1