#Ethiopia | የመንግሥት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አማራጭ ማሸጋገር በሀገሪቱ ስር የሰደደውን የሙስና በሽታ እስከወዲያኛው ለመዝጋት ብቸኛው መንገድ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
ባለፉት ዓመታት ሙስናን ለማስቆም በርካታ ጥረቶች ቢደረጉም፣ ሰዎችን በማሰር ብቻ የሚፈለገው ውጤት እንዳልመጣ ሚኒስትሩ በግልጽ ተናግረዋል።
በተለይም በመንግስት እና በአገልግሎት ፈላጊው መካከል የሚገቡ “ደላሎች” ለችግሩ መስፋፋት ዋነኛ ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሰው፣ የሰውን ንክኪ የሚያጠፋ የዲጂታልና የአንድ መስኮት አገልግሎት የግድ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
አገልግሎት ለማግኘት የሚፈጀው ጊዜ ግልጽ ካልሆነ ነጋዴዎችና ዜጎች ወደ ጉቦ ሊያመሩ እንደሚችሉ የገለጹት ፕ/ር ብርሃኑ፣ ይህም በታማኝነት መስራት የሚፈልጉትን ተስፋ እንደሚያስቆርጥ አስረድተዋል።
የሞባይል አገልግሎት መስፋፋት ተቋማትን ከመገንባት በበለጠ ፍጥነት እና በአነስተኛ ወጪ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለመሆን ትልቅ ዕድል መሆኑንም ጠቁመዋል።
መንግስት የዲጂታል አገልግሎቶችን በስፋት ተደራሽ ካደረገ፣ መውጫና መግቢያ ያሳጣውን ሙስና በመቆጣጠር ረገድ ትልቅ ታሪካዊ እርምጃ እንደሚሆን ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።
Source: GetuTemesgen









No comments yet.