በግፍ ለተገደለው ወጣት ተመስገን ዳንኤል ፍትህ ይስፈን!
ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ማለዳ 2:00 አካባቢ የአቢሲኒያ ባንክ ባልደረባ የሆነው ወጣት ተመስገን ዳንኤል ወደ ሥራ ገበታው እየተሰማራ ባለበት ወቅት በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
ወጣቱ በሽጉጥና በሳንጃ ተወግቶ ለሞት የተዳረገው በአደባባይ እርዳታ እየጠየቀ ቢሆንም፣ በስፍራው የነበረው ማኅበረሰብ በድንጋጤና በዝምታ በመመልከቱ ተገቢውን ድጋፍ ሳያገኝ ነፍሱ እንድታልፍ ተገዷል።
ይህ ዘግናኝ ድርጊት መነሻው ቂም በቀል እንደሆነ በማኅበረሰቡ ዘንድ በስፊው እየተነገረ ይገኛል።
ሟች ተመስገን በቅርቡ በትዳር ከታሰረችው ባለቤቱ ጋር የነበረውን ግንኙነት ያልተቀበለውና ለዓመታት የቀድሞ ፍቅረኛዋ እንደነበር የሚነገርለት ግለሰብ፣ ይህንን አሰቃቂ ጥቃት እንደፈጸመበት መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የአንድ ንጹህ ሰው ሕይወት በዚህ መልኩ በአደባባይ መቀጠፉ እጅግ የሚያሳዝንና የሕግ የበላይነትን የሚፈታተን ተግባር ነው።
በመሆኑም ይህንን ኢ-ሰብአዊ ወንጀል የፈጸሙ አካላት በአስቸኳይ ለሕግ እንዲቀርቡና ለሟች ተመስገን ዳንኤል የሚገባው ፍትህ እንዲሰፍን ጥሪ እናቀርባለን።
የሕግ አስከባሪ አካላት ጉዳዩን በጥልቀት በመመርመር የንጹሃንን ደም በከንቱ የሚያፈሱ ወንጀለኞች ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
በቅርቡ ትዳር መሥርታ የሐዘን ማቅ ለለበሰችው ባለቤቱ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለሥራ ባልደረቦቹ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።gursha
ፍትህ ለተመስገን ዳንኤል!
@Seledadotio

No comments yet.