ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል በሚያልፉ መርከቦች ገቢ እየሰበሰበች ነውኢራን ለዓለም አቀፉ የኢነርጂ አቅርቦት እጅግ ወሳኝ በሆነው…

- Advertisement -
Sidebar AD
ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል በሚያልፉ መርከቦች ገቢ እየሰበሰበች ነው
ኢራን ለዓለም አቀፉ የኢነርጂ አቅርቦት እጅግ ወሳኝ በሆነው በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል በሚያልፉ የጭነት መርከቦች ላይ ከጣለችው አዲስ የጉዞ ቀረጥ የመጀመሪያውን ገቢ መሰብሰቧን ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገለጹ።
የኢራን ፓርላማ ምክትል አፈ-ጉባኤ ሃሚድሬዛ ሃጂ ባባይ ዛሬ እንደተናገሩት፤ ከመተላለፊያ ክፍያው የተገኘው የመጀመሪያው ገቢ በሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ ሂሳብ ውስጥ ገቢ ሆኗል።
ታስኒም የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ ምክትል አፈ-ጉባኤው “ከሆርሙዝ ሰርጥ የመተላለፊያ ክፍያ የተገኘው የመጀመሪያው ገቢ በማዕከላዊ ባንክ ሂሳብ ውስጥ ገብቷል” ብለዋል።
በተጨማሪም የፓርላማ አባል የሆኑት አሊሬዛ ሳሊሚ ለታስኒም እንደገለጹት፤ ባለሥልጣናት በሰርጡ በኩል በሚያልፉ መርከቦች ላይ ክፍያ ማሰባሰብ መጀመራቸውን “አስተማማኝ ከሆኑ ምንጮች” ማረጋገጣቸውን ጠቅሰዋል።
እንደ ታስኒም ዘገባ ከሆነ፤ የቀረጡ መጠን የሚሰላው መርከቦቹ በሚጭኑት የጭነት ዓይነት እና መጠን እንዲሁም በእያንዳንዱ መርከብ ላይ ሊኖር በሚችለው የደኅንነት ስጋት ደረጃ ላይ ተመስርቶ ነው።
ኢራን የቀረጥ መጠኑን የመወሰን እና አሰባሰቡን የመቆጣጠር ኃላፊነትንም ወስዳለች።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1