ሁለቱ ሀገራት ተደራዳሪዎች ልከዋል?

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ኢራን እና አሜሪካ የልዑካን ቡድናቸውን ወደ ፓኪስታን መላካቸው ተዘግቧል።

ከአሜሪካ በኩል የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ የሚመራ፣ ከኢራን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ የሚመራ የተደራዳሪ ቡድን ወደ ኢስላማባድ አቅንቷል ተብሏል።

ባሳለፍነው ሰኞ እለት ሊጀመር የታቀደው ሁለተኛው ዙር ድርድር የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ለመሳተፍ ወደ ፓኪስታን ቢያቀኑም፣ የኢራን ተደራዳሪዎች ባለመገኘታቸው ድርድሩ ሳይካሄድ ቀርቷል።

የኢራኑ መሪ ሞጅታባ ኻሚኒ ግን የኢራን በወቅቱ ተደራዳሪዎች “ወደ ፓኪስታን ማቅናታቸውን” ገልጸው ነበር። ይህ ንግግራቸው ግን መጨረሻው እውነት ሆኖ አልተገኘም።

አሁን ደግሞ የአልጄዚራ ዘገባ እንዳለው ከሆነ፣ ኢራን እና አሜሪካ የልዑካን ቡድናቸውን ወደ ፓኪስታን ልከዋል።

ሁለቱ ሀገራት ከዚህ ቀደም በነበራቸው ውይይት የኑክሌር ምርት ጉዳይ ዋነኛ ማጠንጠኛ ቢሆንም አሁን ደግሞ የሆርሙዝ ሰርጥ የመስተዳደር ኃላፊነት ሌላ አጀንዳ ሆኗል ተብሏል።

በአንፃሩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለ15 የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ለተጨማሪ ቀናት መራዘሙን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #aljazeera
#ThiqahEth


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2