#Ethiopia | የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ7ኛው የምርምር ጉባዔው በተለያየ ዘርፍ የአውቅና ሽልማት ሰጥቷል፡፡ ኮሌጁ የዓመቱ ምርጥ የቀድሞ ተመራቂ (Alumni) ሆኖ የተመረጡት ዶ/ር ዮሐንስ ዘሪሁን ናቸው፡፡
ዶ/ር ዮሀንስ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በሕክምና (Doctor of Medicine) ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን፣ በትምህርትና በተግባር ዘርፎች ከፍተኛ ብቃት አሳይተዋል።
በኢንተርንሺፕ የተግባር ልምምድ ግዜአቸው በተለያዩ ሙያዊ ክፍሎች ሰፊ የክሊኒካል ልምድ በማግኘት፣ በታካሚዎች እንክብካቤ እና በሕክምና ውሳኔ ሂደት ንቁ ተሳትፎ አድርጎዋል።
ከሁሉ በላይ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ያደረጉት አገልግሎት በኒራቅ ጤና ጣቢያ እንደ አጠቃላይ ሐኪም፣ ከመደበኛ ሕክምና ተግባራቸው በተጨማሪ ዝቅተኛ ወጪ ያለው የሚጠቅም ፈጠራ አቀረበዋል፤ ይህም ተጣጣፊ የሆነ በግድግዳ ላይ ተለጣፊ የህጻናት የድንገተኛ አልጋ እና ከርሱ ጋር የተያያዘ የአስተማሚ መቀመጫ፣ ከተቀናጀ መደገፊያ እና የሚነቀል አነስተኛ የሂደት መሳሪያ ትሬይ ጋር የተያያዘ፣ ኮሎስቶሚ አፕሊያንስና የተሻሻለ እስፓይካ ቴብል ነው።
ይህ የፈጠራ ስራ የጤና አገልግሎቱን ተደራሽና እንዲሻሻል አስተዋጻኦ አድርገዋል። ከሕክምና አገልግሎታቸው በተጨማሪ፣ በ3D ፕሪንቲንግ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በመታገዝ በማህበረሰቡ ውስጥ ትምህርትንና ፈጠራን ለማበረታታት “መቅድም ቤተ መፃህፍት እና የፈጠራ ማዕከል” መመስረት ችለዋል።
በሙያቸውና በፈጠራ ስራቸው ከፍተኛ አስተዋጽዎ ላደረጉት ዶ/ር ዮሐንስ ዘሪሁን የዓመቱ ምርጥ አልሙናይ (የቀድሞ ተመራቂ) እንዲሆኑ ተመርጠዋል፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.