ኤምሬትስ ነዳጇን በቻይና ‘ዩዋን’ ልትሸጥ እንደምትችል ለአሜሪካ አስጠነቀቀች

- Advertisement -
Sidebar AD

​ዓለም አቀፉ የንግድ ስርዓት ሊናወጥ ነው!

#Ethiopia | የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ጦርነትና የዶላር እጥረት ካልተቀረፈ፣ ነዳጇን በቻይናው ‘ዩዋን’ (Yuan) ለመሸጥ ልትገደድ እንደምትችል ለአሜሪካ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።

​ ከኢራን ጋር ያለው ውጥረት በባህረ ሰላጤው ሀገራት የዶላር ዝውውርን በማስተጓጎሉ፣ ሀገራቱ አማራጭ ፍለጋ እንዲገደዱ አድርጓቸዋል።

​ አሜሪካ የዶላር አቅርቦትን በፍጥነት ካላመቻቸች (Currency Swap Lines)፣ ኤምሬትስ ወደ ቻይናው ዩዋን እንደምትዞር በግልጽ አስታውቃለች።

​ኤምሬትስ ነዳጇን በዩዋን መሸጥ ከጀመረች፣ ለዓመታት የዘለቀው የዶላር ዓለም አቀፍ የበላይነት ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል።

ተንታኞች እንደሚሉት ኤምሬትስ ዶላርን ሙሉ በሙሉ የመተው ፍላጎት ባይኖራትም፣ ይህ ማስጠንቀቂያ ግን አሜሪካን በፋይናንስና በደህንነት ዘርፍ “እጅ ለማስጠም” እንደ ግፊት መጠቀሚያ እየዋለ ነው። ሆኖም ይህ ሁኔታ ለቻይናው ዩዋን ዓለም አቀፍ ዝና ትልቅ በር የሚከፍት ነው።

ይህ “ዶላርን የመተው” (De-dollarization) ንግግር አሁን ከተራ ወሬ አልፎ ወደ ተግባር እያመራ ይመስላል። የዓለም የንግድ ሚዛን ከአሜሪካ ወደ እስያ (ቻይና) እያጋደለ ነው? ይህ በኢትዮጵያና በሌሎች በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የዶላር ፍላጎት ላይ ምን ተጽዕኖ ይኖረው ይሆን?

​የፔትሮ-ዶላር ዘመን እያበቃ ይሆን? የኤምሬትስ ውሳኔ ዓለምን ያስጨነቀ አጀንዳ ሆኗል!

​#getu #Petrodollar #UAENews #USADollar #ChinaYuan #GlobalEconomy #OilTrade #BreakingNews #DeDollarization #ኤምሬትስ #አሜሪካ #ዶላር #ቻይና #ኢኮኖሚ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2