ኢራን የአየር ክልሏን ክፍት አደረገች!

- Advertisement -
Sidebar AD

* የመጀመሪያው በረራ ተከናወነ

​ከእስራኤልና አሜሪካ ጋር በነበረው ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የኢራን የበረራ አገልግሎት ዛሬ ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ መጀመሩ ተበሰረ። በቴህራን የሚገኘው ኢማም ኾሚኒ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከሁለት ወራት ዝምታ በኋላ በድጋሚ ስራ ጀምሯል።

​ በዛሬው ዕለት ከቴህራን ተነስተው ወደ ቱርክ (ኢስታንቡል)፣ ኦማን (ሙስካት) እና ሳዑዲ አረቢያ (መዲና) በረራዎች ተከናውነዋል።

​በኢራንና አሜሪካ መካከል የተደረሰውን ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ተከትሎ፣ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በከፍተኛ ሁኔታ ቀጥለዋል።

​ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በፓኪስታን ከከፍተኛ አመራሮች ጋር የመከሩ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዙር ከአሜሪካ ጋር የሚደረግ ውይይትም ይጠበቃል።

​የአሜሪካ ልዑክ፦ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አማች ያሬድ ኩሽነር እና ልዩ መልዕክተኛው ስቲቭ ዊትኮፍ ወደ ኢስላማባድ በማቅናት በድርድሩ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

“በረራ መጀመር የሰላም የመጀመሪያው ምልክት ነው። ኢራንና አሜሪካ በፓኪስታን በኩል እያደረጉት ያለው ድርድር ውጤት ካመጣ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ለወራት የቆየው ስጋት ሊቆም ይችላል። በተለይ ያሬድ ኩሽነር በድርድሩ ውስጥ መኖራቸው የትራምፕ አስተዳደር ለጉዳዩ የሰጠውን ትኩረት ያሳያል።”

​ሰማዩ ለሰላም ክፍት ሆኗል!

​#getu #IranNews #MiddleEastPeace #AviationNews #TehranFlight #JaredKushner #Diplomacy #BreakingNews #ኢራን #አሜሪካ #ሰበርመረጃ #በረራ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: