በወላይታ ዞን  በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈበወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ሚያዝያ 15 ቀን 2…

- Advertisement -
Sidebar AD
በወላይታ ዞን  በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ
በወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በጣለዉ ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በዳሞታ ተራራ ግርጌ ባሉ በወሽ ጋሌ እና በኮናሳ ፑላሳ ቀበሌዎች ነው አደጋው ደርሷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን እና የሟቾች ቁጥር ከዚህ ከፍ ሊል ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።
የዞኑ መንግሥት ተጎጂዎች ጎን በመቆም በዘላቂነት የመደገፍና የማቋቋም ሥራ ከወረዳው መንግሥት ጋር ለመሥራት ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
የዝናብ ሁኔታው ከመደበኛ በላይ የመጨመር አዝማሚያ ሊኖር ስለሚችል በዞኑ በካዎ ኮይሻ፣ ኪንዶ ኮይሻ፣ ኪንዶ ዲዳዬ፣ ድጉና ፋንጎ እና አበላ አባያ እንዲሁም ሌሎችም አካባቢዎች የመሬት መንሸራተት፣ ናዳ እና የወንዝ ሙላት ሊያጋጥም ስለሚችል ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1