ኑቢራ የእናቶችና ህፃናት ህክምና ማዕከል ተመረቀ።

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia |​ በአምስት ሀኪም ጓደኛማቾች ጥረት በ2015 ዓ.ም የተመሰረተው ኑቢራ የእናቶችና ህፃናት ህክምና ማዕከል፣ እራሱን በማሳደግ በዛሬው እለት ተመርቋል።

ተቋሙ ከ40 በላይ የሚሆኑ ስፔሻሊስትና ሰብ-ስፔሻሊስት ሃኪሞችን በማደራጀትና ካፒታሉን በማሳደግ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት ወደሚሰጥ የጤና ማዕከልነት ተሸጋግሯል።

በማዕከሉ ምረቃ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጄ ድጉማ፣ በርካታ ከፍተኛ ባለሙያዎች በቋሚነትና በትርፍ ጊዜያቸው እንዲሰሩ መደረጉ የህክምናውን ጥራት ከፍ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።

ማዕከሉ ደረጃቸውን የጠበቁ ከ30 በላይ ተኝቶ መታከሚያ አልጋዎችና በአንድ ጊዜ ሶስት የቀዶ ህክምና አገልግሎቶችን መስጠት የሚችሉ ክፍሎችን አደራጅቶ ስራ መጀመሩ ተነግሯል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ኑቢራ የጤና ማዕከል ከታዋቂዎቹ ጥንዶች አርቲስት ተስፋለም ታምራት እና አርቲስት ቃልኪዳን አበራ ጋር ለሁለት ዓመታት የሚቆይ የአምባሳደርነት ስምምነት ተፈራርሟል።

“ኑቢራ” በአፋን ኦሮሞ “እኛ ጋር” ማለት ሲሆን፣ ማዕከሉ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለማግኘት ወደ እኛ ኑ በማለት ጥሪውን አስተላልፏል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2