አልቲማ ሪል እስቴት ቤቶችን ማስረከብ ጀመረ

- Advertisement -
Sidebar AD

* እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ቅናሽም አዘጋጅቷል

#Ethiopia | ​አልቲማ ሪል እስቴት (Ultima Real Estate) በመስቀል ፍላወር አካባቢ ያስገነባውን ዘመናዊ ባለ 12 ፎቅ ((G+12) ዘመናዊ የመኖሪያ ህንፃ) ግንባታውን በሁለት ዓመት ብቻ አጠናቆ ለባለቤቶቹ ማስረከብ መጀመሩን በዛሬው ዕለት በይፋ አስታውቋል።

​ህንፃው በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃ ሲሆን፣ አስተማማኝ የመኪና ማቆሚያ፣ የከርሰ ምድር ውሃና ጀነሬተር የተሟላለት ነው።

​ የርክክብ መርሃ ግብሩን በማስመልከት በቱሊፕ ሆቴል ጀርባ ከዛሬ ሚያዝያ 17 እስከ ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም. ለ5 ቀናት የሚቆይ ኤክስፖ ተከፍቷል።

ጓደኛማቾቹ፤ የአልቲማ ሪልእስቴት ባለቤቶቹ (ኢንጂነር ዮሴፍ ፍቃዱና ኢንጂነር ሳሙኤል ፅጋብ)
Friends Engineering – ዛሬ ጥርስ በጥርስ ሆነዋል። ምክንያታቸውን ተጠየቁ – “አልቲማ በማስረከብ የማይታማ” በማለት ሣቃቸውን እንደዥረት አፈሰሱት።

እውነት ነው!

ኢንጂነር ሣሙኤል እንዳብራሩት፤
“የከተማችን የሪል እስቴት አልሚዎች ከገዢዎች ጋር በጊዜ ባለማስረከብ የሚጓተቱበት ምክንያት ነው። አልቲማ ይህንን መደነቃቀፍ እንዲኖር አንፈቅድም። ደምበኞቻችን ቋሚ ምስክሮቻችን ናቸው። ለዚያም ነው አልቲማ በማስረከብ የማይታማ የምንለው። ይህ ከቃል በላይ ነው። አልቲማ ሥራችን ከቃል በላይ ነው” ብለዋል።

በኤክስፖው ወቅት ቤቶችን ለመግዛት ለሚመዘገቡ ደንበኞች ለእያንዳንዱ ቤት እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ልዩ ቅናሽ ተዘጋጅቷል።

​ “ፕሪሚየም ሳይት” የተባለውን 4ኛ አዲስ ፕሮጀክት ያስተዋወቁ ሲሆን፣ ደንበኞች በ5 በመቶ ቅድመ ክፍያ ብቻ መመዝገብ ይችላሉ።

በሪል እስቴት ዘርፍ ትልቁ ፈተና ቃልን ጠብቆ በወቅቱ ማስረከብ ነው።

አልቲማ ባለፉት ሦስት ዓመታት ሁለት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ማስረከቡ በዘርፉ ታማኝነትን እያተረፈ መሆኑን ያሳያል። በተለይ በ5% ቅድመ ክፍያ አዲስ ቤት መመዝገብ መቻሉ ለብዙዎች ትልቅ ዕድል ነው።

​ ኤክስፖውን ለመጎብኘት፦

​ መስቀል ፍላወር፣ ቱሊፕ ሆቴል ጀርባ

​ እስከ ሚያዝያ 21/2018 ዓ.ም.

​ቤትዎን በቅናሽ ለመግዛት አሁኑኑ ወደ ኤክስፖው ጎራ ይበሉ!

አልቲማ ሪል እስቴት ከዚህ ቀደም የመጀመሪያ ፕሮጀክቱን በላንቻ አርባ ምንጭ አሣ ቤት ፊት ለፊት ገንብቶ ማጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ያስረከበው ህንፃ በኩባንያው ታሪክ ሁለተኛው የተሳካ ርክክብ መሆኑ ተገልጿል።

​#getu #UltimaRealEstate #AddisAbabaHousing #EthiopiaRealEstate #HomeOwnership #PremiumSite #DiscountOffer #RealEstateExpo #አልቲማሪልእስቴት #ቤት #አዲስአበባ #ቅናሽ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: