* ፕሬዝዳንት ትራምፕ በድንገት ተወሰዱ
#Ethiopia | ዛሬ ሌሊት በዋሽንግተን ሒልተን ሆቴል በተካሄደው የዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች የእራት ግብዣ (White House Correspondents’ Dinner) ላይ ያልተጠበቀ የተኩስ ድምፅ በመሰማቱ ከፍተኛ ግርግር ተፈጥሯል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በደህንነት አካላት ጥበቃ ተደርጎላቸው በአስቸኳይ ከቦታው እንዲወጡ ተደርጓል።
እንደ የጸጥታ አካላት ገለፃ ከ7 እስከ 8 የሚደርሱ የጥይት ድምፆች ተሰምተዋል። በወቅቱ የነበሩ ታዳሚዎች በድንጋጤ ከጠረጴዛ ስር ተሸሽገው ነበር።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በራሳቸው የትሩዝ ሶሻል (Truth Social) ገፃቸው ላይ “ተኳሹ በቁጥጥር ስር ውሏል” ሲሉ አረጋግጠዋል። የደህንነት መስሪያ ቤቱም አንድ ግለሰብ መያዙን ገልጿል።
ፕሬዝዳንቱ፣ ቀዳማዊት እመቤቷና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት (የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ካሽ ፓቴልን ጨምሮ) በሰላም ከቦታው መውጣታቸው ታውቋል።
ትራምፕ “ዝግጅቱ መቀጠል አለበት” (Let the show go on) የሚል አስተያየት የሰጡ ቢሆንም፣ የጸጥታ አካላት ግን ጥብቅ ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።
ይህ ክስተት አሜሪካ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ውጥረትና የደህንነት ስጋት ዳግም ያሳየ ነው። የጋዜጠኞች የእራት ግብዣ ላይ እንዲህ ያለ ድፍረት የተሞላበት ሙከራ መደረጉ አፍን በእጅ አስከድኗል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሰላም ቢወጡም የደህንነት አካላቱ እንዴት እንዲህ ያለ ክፍተት እንደተፈጠረ ትልቅ ምርመራ ይጠብቃቸዋል።
ዲፕሎማሲውና ፖለቲካው በጥይት ድምፅ ታውኳል!
የዓለም ዓይኖች ወደ አሜሪካ ዞሯል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getu #TrumpNews #BreakingNews #WhiteHouseDinner #WashingtonDC #TrumpSafety #SecretService #GlobalNews #ትራምፕ #ሰበርመረጃ #ዋሽንግተን #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen
Source: GetuTemesgen









No comments yet.