ሞዴል ናርዶስ አበበ የ2026 ተፅዕኖ ፈጣሪ በመባል በሁለት ዘርፎች አሸነፈች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ መድረኮች በመወከል የምትታወቀው ድንቋ ሞዴል ናርዶስ አበበ፣ በጋና በሚገኘው “ዘ ስትሪት ኦፍ ጎልድ ፋውንዴሽን” (The Street of Gold Foundation) በተዘጋጀው ታላቅ መርሃ ግብር የሁለት ወርቅ ዋንጫዎች ባለቤት መሆኗ ተበሰረ።

​ ለሽልማት ያበቃት ዋና ምክንያት፦

​ በቲክቶክ (TikTok) ገጿ ከ700 ሺህ በላይ ተከታዮችን በማፍራት፣ ያላትን ተሰሚነት ድጋፍ ለሚሹ ህፃናት፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞች እርዳታ በመሰብሰብ ለበጎ ተግባር ማዋሏ።

​ዘር፣ ቀለም እና ሃይማኖት ሳትለይ ድጋፍ የሚሹ ኢትዮጵያውያንን መርዳቷና በካንሰር እንዲሁም በኦቲዝም የተጠቁ ወገኖችን በፍቃደኝነት ማገልገሏ።

​በሞዴሊንግ ዘርፍ ኢትዮጵያን ወክላ በሚስ-አፍሪካ (Miss Africa) ውድድር እስከ መጨረሻዎቹ አምስት (Top 5) ውስጥ በመግባት ያሳየችው ብቃት።

​ሽልማቱ የተዘጋጀው በጋናው “ዘ ስትሪት ኦፍ ጎልድ ፋውንዴሽን” ሲሆን፣ በአዲስ አበባ በተካሄደው 11ኛው አውደ ርዕይ ላይ ናርዶስን ጨምሮ 6 ኢትዮጵያውያን ሴቶች ተሸላሚ ሆነዋል።

​አጠቃላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 20 ሴቶች በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በአርትና በበጎ ስነ-ምግባር ዘርፍ ላሳዩት ተነሳሽነት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

ናርዶስ የአራት ልጆች እናትና ባለትዳር ሆና፣ ቤተሰቧን እየመራች እንዲህ ያለ ሀገራዊና አህጉራዊ ተፅዕኖ መፍጠሯ የሚደነቅ ነው። በቲክቶክ የምናሳልፈው ጊዜ እንዲህ ለበጎ አላማ ሲውል ውጤቱ የሀገር ኩራትና የብዙዎች ተስፋ ይሆናል።

በቅርቡ ደግሞ ‘ሆፕ ፎር ኦል’ (Hope For All) ከተባለ ድርጅት ጋር በመሆን ለእናቶችና ህፃናት የምታደርገው ድጋፍ ይጠበቃል።

​ውበት ከበጎነት ጋር ሲደመር ለሀገር ኩራት ነው!

​#getu #NardosAbebe #Influencer2026 #EthiopianModels #StreetOf Gold #WomenEmpowerment #Humanitarian #AddisAbabaEvents #AfricaAwards #ናርዶስአበበ #ተፅዕኖፈጣሪ #በጎአድራጎት #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1