ዮሚፍ ቀጄልቻ ከ2 ሰዓት በታች በመግባት የኢትዮጵያን ሪኮርድ ሰበረ
#Ethiopia | የዛሬው የለንደን ማራቶን በዓለም አትሌቲክስ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ ቀን ሆኖ ውሏል። በወንዶች ማራቶን ለመጀመሪያ ጊዜ የሁለት ሰዓት አጥር የተሰበረበትና የኢትዮጵያ የምንግዜም የፍጥነት ክብረ ወሰን በዮሚፍ ቀጄልቻ የተሻሻለበት ታሪካዊ ውድድር ተካሂዷል።
የለንደን ማራቶን 2026 አስደናቂ ውጤቶች
አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በማራቶን የመጀመሪያ ተሳትፎው 1:59:41 በሆነ አስገራሚ ሰዓት በመግባት፣ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች የጨረሰ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሆኗል።
አዲስ የዓለም ሪኮርድ
ኬንያዊው ሰባስትያን ሳዌ በ1:59:30 አንደኛ በመውጣት አዲስ የዓለም ሪኮርድ ሲያስመዝግብ፣ ዮሚፍ በሰከንዶች ልዩነት ሁለተኛ ወጥቷል።
የኪፕቱም ሪኮርድ ተሰበረ
የዛሬው ውድድር ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ የወጡት አትሌቶች በሙሉ፣ ኬልቪን ኪፕቱም ይዞት የነበረውን 2:00:35 የዓለም ሪኮርድ አሻሽለውታል።
የኢትዮጵያውያን ተሳትፎ፦ ታምራት ቶላ (5ኛ)፣
ደረሰ ገለታ (6ኛ) እና አዲሱ ጎበና (7ኛ) በመሆን ውድድሩን በከፍተኛ ፉክክር አጠናቅቀዋል።
የኢትዮጵያ የምንግዜም ፈጣን 5 የማራቶን ሰዓቶች (ከዛሬው በኋላ)፦
ዮሚፍ ቀጄልቻ (1:59:41) – 2026 ለንደን ማራቶን 🥇 (አዲስ ሪኮርድ)
ቀነኒሳ በቀለ (2:01:41) – 2019 በርሊን ማራቶን
ሲሳይ ለማ (2:01:48) – 2023 ቫሌንሲያ ማራቶን
ደሬሳ ገለታ (2:02:38) – 2024 ቫሌንሲያ ማራቶን
ብርሀኑ ለገሰ (2:02:48) – 2019 በርሊን ማራቶን
ዮሚፍ ዛሬ የሰራው ስራ እጅግ የሚደንቅ ነው። ገና በመጀመሪያ ተሳትፎው የቀነኒሳንና የሌሎችን ታላላቅ አትሌቶች ሰዓት አሻሽሎ ከሁለት ሰዓት በታች መግባቱ፣ ወደፊት በማራቶን የሚኖረውን የበላይነት ያረጋገጠበት ነው። ዛሬ ለንደን ላይ በትዕግስት አሰፋና በዮሚፍ ቀጄልቻ ድል የኢትዮጵያ ስም በአለም ፊት በደመቀ ሁኔታ ታውጇል!
ከሁለት ሰዓት በታች!
ዮሚፍ ቀጄልቻ አዲሱ የኢትዮጵያ የማራቶን ንጉሥ!”
#EthiopianAthletics #YomifKejelcha #LondonMarathon2026 #NewRecord #MarathonHistory #TigistAssefa #EthiopiaPride #ዮሚፍቀጄልቻ #ለንደንማራቶን #ሰበርዜና #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen

Source: GetuTemesgen









No comments yet.