ከውጪ ሀገር ዜጋ ላይ የስርቆት ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ ተመሰረተበት።

- Advertisement -
Sidebar AD

ተጠርጣሪው የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ 00672 በሆነ ዴ.ኤክስ ተሽከርካሪ የታክሲ አገልግሎት በመስጠት የሚተዳደር ነው፡፡

ሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ/ም የተለመደውን የታክሲ አገልግሎት ዶ/ር ጣሂር ሀሚድ ለተባሉ የሳውዲ ዜግነት ላላቸው ግለሰብ ከቦሌ ኤርፖርት በመጫን ጉዞውን ወደ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 2 አይሻ መስኪድ እየተባለ ወደ ሚጠራው አካባቢ ያደርጋል፡፡

ግለሰቡም ካሰቡበት ቦታ ደርሰው ሂሳብ ከፍለው ከታክሲው ይወርዱና ተሽከርካሪውን ይሸኛሉ፤ ነገር ግን ፖርሳቸው ባረጋገጡበት ወቅት ይዘውት የነበረው 3ሺህ የሳውዲ ሪያል የተሰረቀባቸው መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

‎የግል ተበዳይም የተፈፀመባቸው ወንጀል በቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለላንቻ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በማመልከታቸው ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ/ም ገንዘቡን ወደ ኢትዮጵያ ብር እንደመነዘረው በቁጥጥር ስር ሊያውለውም ችሏል፡፡

‎የታክሲ ትራንስፖርት የሚጠቀሙ ተገልጋዮች ህጋዊነት ያላቸውን እና በጥሪ ማዕከሎች የሚገኙ አገልግሎቶችን መጠቀም እንደሚገባቸውም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል፡፡

Addis Ababa police





Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: