ተጠርጣሪው የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ 00672 በሆነ ዴ.ኤክስ ተሽከርካሪ የታክሲ አገልግሎት በመስጠት የሚተዳደር ነው፡፡
ሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ/ም የተለመደውን የታክሲ አገልግሎት ዶ/ር ጣሂር ሀሚድ ለተባሉ የሳውዲ ዜግነት ላላቸው ግለሰብ ከቦሌ ኤርፖርት በመጫን ጉዞውን ወደ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 2 አይሻ መስኪድ እየተባለ ወደ ሚጠራው አካባቢ ያደርጋል፡፡
ግለሰቡም ካሰቡበት ቦታ ደርሰው ሂሳብ ከፍለው ከታክሲው ይወርዱና ተሽከርካሪውን ይሸኛሉ፤ ነገር ግን ፖርሳቸው ባረጋገጡበት ወቅት ይዘውት የነበረው 3ሺህ የሳውዲ ሪያል የተሰረቀባቸው መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
የግል ተበዳይም የተፈፀመባቸው ወንጀል በቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለላንቻ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በማመልከታቸው ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ/ም ገንዘቡን ወደ ኢትዮጵያ ብር እንደመነዘረው በቁጥጥር ስር ሊያውለውም ችሏል፡፡
የታክሲ ትራንስፖርት የሚጠቀሙ ተገልጋዮች ህጋዊነት ያላቸውን እና በጥሪ ማዕከሎች የሚገኙ አገልግሎቶችን መጠቀም እንደሚገባቸውም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል፡፡
Addis Ababa police


Source: Yeneta Tube









No comments yet.