የጨፌ ወጣቶች ሁለገብ ህብረት ስራ ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ሰኚ ኢደሹ በአንዳፍታ ላይ ተሳዳቢ ነህ ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል።
ስድብ ተሳድቤ አላውቅም ያለው ሰኚ ስድቦቼ በሙሉ ዘመናዊ አይደሉም ባህላዊ ናቸው ብሏል። ሁለት አይነት ስድብ አለ ባህላዊ እና ዘመናዊ፣ በህይወቴ ተሳድቤ አላውቅም። ባህላዊ ሀገር በቀል ስድብ መሳደብ ስድብ አይደለም። “ባለጌ፣ ወርጋጥ፣ ልክስክሳም፣ ልፋጫም” ማለት ስድብ አይደለም ብሏል። በእናት፣ በብሄር፣ በኃይማኖት የምትሳደቡ ከሆነ ዘመናዊ ስድብ ነው እናንተ ተሳዳቢ ናችሁ ሲል ተናግሯል። በቲክቶክ ላይ የሚለቀቁ የኔ ቪዲዮዎች የኔ ጠንከር ያለ ምክረ ሃሳብ ነው እንጂ ስድብ አይደለም ብሏል።
Source: FastMereja









No comments yet.